ምርጫ ቦርድ ለአዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህጋዊ ሰውነት  ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለሀገር አቀፍና ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አስታወቀ።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠው ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲና ለብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተሰኙ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ ለተሰኘ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል።
ቦርዱ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ያከናወነው የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011  በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መሆኑ ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply