ምርጫ ቦርድ አብን ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሄድበትን ጊዜ በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ አሳሰበ

ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሄድበትን ቀን በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ አሳሰበ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በድጋሜ የሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባዔን አስመልክቶ ውሣኔ ማሳለፍኑ አስታውቋል።

ቦርዱ ዛሬ እንዳስታወቀው አብን እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ድረስ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርግ በቦርዱ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፤ ፓርቲው በቦርዱ ውሣኔ መሠረት ጉባዔውን ሳያካሄድ የተሰጠው ጊዜ ገደብ ማለፉን ገልጿል። በመሆኑም አብን ጠቅላላ ጉባዔውን መቼ ለማድረግ እንደወሠነ ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

በተጨማሪም ቦርዱ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ጨምሮ ሌሎች የጠቅላላ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቶችን እንዲያሳውቅ ውሳኔ ማስተላለፉንም ገልጿል።

እንዲሁም የፓርቲው የጠቅላላ ጉባዔ አባላት የሚጠሩበትን ሁኔታ በተመለከተ በፓርቲው የተሰጡ የፓርቲው ውሣኔዎችን እንዲያቀርብ እና እስካሁን ያለውን ክዋኔያውን እንዲያብራራ፣ በተጨማሪም ሌሎች የጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ጉባዔ ዝግጅቶችን ለቦርዱ እንዲገልጽ ቦርዱ መወሰኑንም ጨምሮ አስታውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የጠቅላላ ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ ሐምሌ 24 ቀን 2014 እንዳስታወቀው፤ ኮሚቴው ሥራውን ያጠናቀቀ ሲሆን ፓርቲው ያጋጠመው የፋይናንስና ሎጀስቲክ ውስንነቶች እንደተስተካከሉ ጉባኤውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያካሄዱ መግለጹ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply