You are currently viewing ምርጫ ቦርድ አቶ አምሃ ዳኘው ለባልደራስ ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡበት ሂደት ህጋዊ መሆኑን በመቀበል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

ምርጫ ቦርድ አቶ አምሃ ዳኘው ለባልደራስ ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡበት ሂደት ህጋዊ መሆኑን በመቀበል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

ምርጫ ቦርድ አቶ አምሃ ዳኘው ለባልደራስ ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡበት ሂደት ህጋዊ መሆኑን በመቀበል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አቶ አምሃ ዳኘው ለባልደራስ ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡበት ሂደት መመሪያውን የተከተለ እና ህጋዊ መሆኑን በመቀበል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን በደብዳቤው አስታውቋል። ቦርዱ ኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ውሣኔውን ባሳወቀበት ደብዳቤው እንዳመለከተው የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤን ለመጥራት የሄደበት ሂደት የተሟላ በመሆኑ ተቀብሎታል። ስለሆነም ቦርዱ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በ15/12/2014 ዓ.ም. ለሶስተኛ ጊዜ ተጠርቶ 12 አባላት በተገኙበት በሙሉ ድምፅ አቶ አምሀ ዳኜው ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሆኑ ያሳለፈውን ውሣኔ ተቀባይነት እንዳገኘ በመግለጽ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኜው ናቸው ሲል ወስኗል። በተጨማሪም ፓርቲው በ29/01/2015 ዓ.ም. ለማድረግ ያቀደው ጠቅላላ ጉባኤ ቀኑ ያለፈ በመሆኑ በደንቡ መሠረት ተለዋጭ ቀን በመቁረጥ ለቦርዱ በማሳወቅ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያካሂድ ቦርዱ ውሳኔውን ለፓርቲው አሳውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply