ምርጫ ቦርድ ፓርላማው ያፀደቀለትን 304 ሚሊዮን ብር አለማግኘቱን አስታወቀ፡፡በ2013 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ በቦርዱ ውሳኔ ምርጫ ባልተካሄደባቸውና በድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በቤ…

ምርጫ ቦርድ ፓርላማው ያፀደቀለትን 304 ሚሊዮን ብር አለማግኘቱን አስታወቀ፡፡

በ2013 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ በቦርዱ ውሳኔ ምርጫ ባልተካሄደባቸውና በድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች፣ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫው እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

በስድስተኛው ዙር አገራዊ ምርጫ፣ ምርጫ ያልተካሄደባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች 96 ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ትግራይ 38፣ ኦሮሚያ 8፣ አማራ 19፣ አፋር 9፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 19፣ ደቡብ 2፣ እንዲሁም ሶማሌ 1 ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ምርጫዎች ያልተካሄዱት በፀጥታ ችግር እንደሆነ ባለፈው ዓመት ቦርዱ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ቦርዱ በተያዘው 2016 የበጀት ዓመት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ይፋ ባደረገው ፕሮገራም ከአራቱ ክልሎች ውጪ ምርጫው ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ለማካሄድ የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ አለመሆኑን የቦርዱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ምርጫውን ለማካሄድ ስራዎቹ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ቢሆኑም በጀቱ እስካሁን አልተለቀቀም ተብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply