ምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የኦነግ ወታደሮች ግድያ መፈጸማቸው ተገለጸ።        አሻራሚዲያ    ህዳር፡-21/03/13/ዓ.ምባህርዳር ምንጫችን…

ምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የኦነግ ወታደሮች ግድያ መፈጸማቸው ተገለጸ። አሻራሚዲያ ህዳር፡-21/03/13/ዓ.ምባህርዳር ምንጫችን…

ምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የኦነግ ወታደሮች ግድያ መፈጸማቸው ተገለጸ። አሻራሚዲያ ህዳር፡-21/03/13/ዓ.ምባህርዳር ምንጫችን ከቦታው በስልክ እንደገለጹልን በምስራቅ ወለጋ በሊሙ ወረዳ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የኦነግ ወታደሮችበጭነት መኪናበመግባት ግድያ ፈጽመዋል፡፡ ከለሊቱ ስድስት 6 ስዓት አከባቢ አርቁምቢ መንደር ውስጥ የኦነግ ወታደሮች በመኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት ይሎክሳሉ ይህንን የተመለከቱ የመንደሯ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት በብዛት ሲወጡ የኦነግ ወታደሮች በጅምላ በጥይት ደብድበዋቸዋል። በምስራቅ ወለጋ በሊሙ ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በተከፈተባቸው ተኩስ ምክንያት ብዙዎች ለህልፈትና ተዳርገዋል ነው ያሉትምንጫችን፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት እስካሁን ማንም የመንግስት አካላት እንዳልደረሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ስለጉዳዩ በአካባቢው ለሚገኙ የስራ ሀላፊዎች ተደውሎ ቢነገራቸውም ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። ይህ የሆነበት ደግሞ በአካባቢው የሚገኙ የስራ አመራሮች ተባባሪ ስለሆኑ ነው ብለዋልመረጃውን ያደረሱን የአካባቢው ምንጫችን፡፡ በመጨረሻም የጸጥታ ሃይል ገብቶ ከጭፍጨፋ እንዲታደጋቸውና መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply