You are currently viewing ምኒልክ እና ጣይቱ የሌሉበት ትያትር ተሰርቶ ተቃውሞ ገጠመው! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣        በመጪው ሀሙስ ለሚከበረው 127ኛው የዓድዋ በዓል በመስቀል አደባባይ ሊ…

ምኒልክ እና ጣይቱ የሌሉበት ትያትር ተሰርቶ ተቃውሞ ገጠመው! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በመጪው ሀሙስ ለሚከበረው 127ኛው የዓድዋ በዓል በመስቀል አደባባይ ሊ…

ምኒልክ እና ጣይቱ የሌሉበት ትያትር ተሰርቶ ተቃውሞ ገጠመው! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በመጪው ሀሙስ ለሚከበረው 127ኛው የዓድዋ በዓል በመስቀል አደባባይ ሊቀርብ ባለፈው ሀሙስ ከሰዓት ለግምገማ በሀገር ፍቅር ቴአትር ለሚመለከታቸው ክፍሎች ሲቀርብ ትያትሩ ላይ ዋንኞቹ የዓድዋ ጦርነት መሪዎች ዳግማዊ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ የሌሉበት መሆኑ በዚያው ትያትር ላይ በሚሰሩት አርቲስቶች ጭምር ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል ። ይኸው ትያትር ከየትያትር ቤቱ በተውጣጡ እና ከየክፍለ ከተማው በመጡ ሙያተኞች የተመደረከ ሲሆን አሰሪው ደግሞ የአዲስ አበባ ባሕል ፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ነው ። አርቲስቶቹ እንዴት ምኒልክና ጣይቱ የሌሉበትን ትያትር አምነው እንደሰሩ ግልጽ ባይሆንም በወቅቱ ግምገማውን ለሚመሩ ሰዎች ይህ አይነቱን ትያትር ለምን መስራት እንዳስፈለገ እና ተገቢ አለመሆኑን በተቃውሞ መልክ አቅርበዋል ። ይሁንና ይኸው ስራ በመጪው ሀሙስ መቅረቡ እንደማይቀር ፣ አርቲስቶቹ የጠየቁት አይነት ሌላም ስራ እንዳለ ነው የተነገራቸው ። ምኒልክና ጣይቱ የሌሉበትን የዓድዋ ድል ትያትርን እናያለን ማለት ነው ። ሄደን ሄደን እዚህ ደርሰናል ። ትናንት አልፎ ዛሬን አይተናል ። ነገም ደግሞ የራሱን ታሪክ ይዞ ይመጣል ። በእውነት በሀገሬ በሆነውና እየሆነ ባለው ሁሉ ልቤ ተሰብሯል ።ቀደም ብለው ተፈጥረው ይህን ጊዜ ሳያዩ የሞቱ እጅግ እድለኞች ናቸው ። ካለነው ይልቅ በሞቱት እቀናለሁ ። ኢትዮጵያ ሆይ እግዚአብሔር ይሁንሽ ። ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ትክለአረጋይ የፃፈው 👆 “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply