በዋነኝነት በወቅቱም ሀያል የነበሩትና ማን ዩናይትድ በስፋት ደግሞ አርሰናል በኢንቪንሲብል ሲዝኑ ብዙዎችን መማረክ ችለዋል በተለይ የሬይ ፓርለርና የነ ቫንኒስተልሮይ ፍጥጫ እንዴት ይረሳል ኪን ከ ቬራ፤ ኔቭል ከነ አሽሊ፤ ኮል ኦነሪ ከቫን ኒስተልሮይ፤ ከምንም በላይ ከጨዋታው በፊትና በኋላ በሰሩና በፕሮፌሰሩ መሀከል ያሉ ሽንቆጣዎች ልዩ ትኩረት በሚስብ መልኩ እንድናስታውስ በጥሩ ትውስታ አሳድገውናል እስቲ የናንተንም ትውስታ አጋሩን
ለረጅም ጊዜ የሁለቱ ቡድኖች ፍጥጫ በደጋፊው ልብ ከፍ ያለ ቦታ ይያዝ እንጂ የቡድኖቹ የፉክክር ጨዋታ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም ወይ አንደኛው የተሻለ የበላይነት ኖሮት አለዚያም ሁለቱም በጥሩ አቋም ላይ እያሉ የተደረገ ጨዋታ ለማስታወስ ከአስር አመት በላይ ወደ ኋላ መመለስ የግድ ይለናል እጅግ በአስገራሚ የውጤት ግስጋሴ ላይ የሚገኙት የአርቴታ መድፈኞች ሂደቱን አምነው ለአመታት የተናፈቀው አርሰናል በግሩምና አሳማኝ ጨዋታ መደፋቸውን ስለው ከእቅድ በላይ በመተኮት ለናፈቁት የሊግ ክብር አልመዋል እስካሁን የተደናቀፉት ኦልድትራፎርድ ብቻ ነው በአንጻሩ አጀማመሩ ከባድ የነበረው ቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ቴን ሀግ ነገሮችን ለማስተካከል ጊዜ ቢፈልግም ወደ ትክከለኛው ትራክ የገቡ መስለዋል
ወሳኙ ካዝሜሮ እጅግ በቀሽም ውሳኔ በፓላሱ ጨዋታ በተመለከተው ቢጫ ካርድ የዛሬዉ ጨዋታ የሚዘለው መሆኑ ለብዙ ዩናይትዳዊያን ስጋት ቢጤ ገብቷቸዋል በኦልድትራፎርዱ ጨዋታ ፓርቴን ያጡት አርሰናሎች ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ በጥሩ ልበ ሙሉነት ዩናይትድን ለመበቀል ጭምር ያስተናግዳሉ ማሸነፍ ከቻሉ ከተከታዮቻቸው ያላቸውን ልዩነት ቢያንስ ማስጠበቅ ሲችሉ ሲቲ በተኩላዎቹ ነጥብ ከጣለ ዋንጫው ላይ አንድ እጃቸውን ያሳርፋሉ።
እናንተም ይህን ተጠባቂ ጨዋታ በቲፎዞ ግብግብ እየተተራረብን እየተሸነቋቆጥን ከተጋበዙት ደጋፊዎች ጋር ግሩም ጊዜ ይኖረናል በቲክቶክም በቀጥታ ቀጠሮ ይኑረን 1:00 በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንገናኝ
Source: Link to the Post