ምንም አይነት የሚያሰጋ የጸጥታ ችግር ባለመኖሩ ማህበረሰቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን መጀመሩን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስታወቀ፡፡

በህግ ማስከር ዘመቻው አንድ አንድ አካባቢዎች ላይ ችግሮች ተፈጥረው እንደነበር ተገልጿል፡፡የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወቀ ወርቁ ለአሐዱ እንደተናገሩት አሁን ላይ የሚያሰጋ የጸጥታ ችግር ባለመኖሩ ማህበረሰቡ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ የሚሆንበቸውን የስራ ዘርፎችን ክፍት በማድረግ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ እንዲመለስ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባደረገው ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩን የተናገሩት አቶ አወቀ የጤና እና ሌሎች የመሰረታዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ፣ የመስኖ ስራ፣ የተፈጥሮ ልማትን የማስጀመር እና ሌሎች የግብርና ስራ ላይም እንደቀድሞ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡እያንዳንዱ ግለሰብ ችግሮችን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት ለጸጥታ ኃይሉ ተባባሪ በመሆን ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

***************************************************************************

ቀን 27/04/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply