ምንም አይነት የአልኮል ምርት የማይሸጥበት ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት ተመረቀ።በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው በአይነቱ የተለየው ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት በዛሬው እለ…

ምንም አይነት የአልኮል ምርት የማይሸጥበት ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት ተመረቀ።

በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው በአይነቱ የተለየው ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት በዛሬው እለት ተመርቋል።

የሼባ አቬሽን እንዲሁም የሼባ ቪሌጅ ሪልስቴት እህት ኩባኒያ የሆነው ሼባ ቬሌጅ ሪዞርት በዛሬው እለት ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት የማረፍያ ቤቶቹ ለቤተሰብ ምቹ ሆነው የተገነቡ ቤቶች ናቸው ተብሏል።

ለቱሪስቶች በጥምረት እንዲሁም በቤተሰብ መልክ ሆነው ለሚመጡ ዜጎች ሳይነጣጠሉ አንድ ላይ እንዲሆኑ ተደርገው የተገነቡ ዘመናዊ ቤቶች መሆናቸውም ተገልጿል።

የሼባ ቪሌጅ ሪዞርት ቤቶች ባለ ሶስት እና ባለ አምስት መኝታ ቤት ያላቸው እና ሙሉ የቤት መገልገያ እቃዎች የተሟላላቸውም ናቸው።

የቢሾፍቱ ከተማ ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደጀኔ በጅሩ ከተማውን የቱሪስት የስበት ማዕከል ለማድረግ ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።
ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት ለቢሾፍቱ ከተማ ተጨማሪ ውበት ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል።

ቢሾፍቱ ከተማን የምሥራቅ አፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ተቋማትን የማስፋፋቱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማዋ ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ በድሩ ገልጸዋል፡፡
በ25 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና 350 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ሪዞርቱ ምንም ዓይነት አልኮል የማይሸጥበት ሲሆን 20 ባለ 5 እና ባለ 3 ዘመናዊ ክፍሎች ( ቪላ) ፣ ዘመናዊ መዋኛ ስፍራ፣ የህጻናት መዝነኛ፣የስብሰባ አዳራሽና ዘመናዊና ባሕላዊ ምግብ ቤቶችን የያዘ መሆኑም ተገልጿል።
ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት አሁን ባስገነባው አዲስ የመዝናኛ ስፍራ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል እንደፈጠረም ገልጿል።
ቢሾፍቱ ላይ የተገነባው ሼባ ቪሌጅ ሪዞርት የአልኮል መጠጥ የማይሸጥበት ብቸኛ ቦታ መሆኑንም ተነግሯል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply