You are currently viewing #ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ /አረርቲ ከተማ/        ኑ ከተማችን በጋራ  እንገባ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ካሉ 24  ወረዳዎች አንዷ ምንጃር ሸንኮራ ስትሆን ከአ…

#ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ /አረርቲ ከተማ/ ኑ ከተማችን በጋራ እንገባ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ካሉ 24 ወረዳዎች አንዷ ምንጃር ሸንኮራ ስትሆን ከአ…

#ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ /አረርቲ ከተማ/ ኑ ከተማችን በጋራ እንገባ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ስር ካሉ 24 ወረዳዎች አንዷ ምንጃር ሸንኮራ ስትሆን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ 133 ኪሎ ሜትር ከዞኑ ዋና ከተማ 263 ኪሎ ሜትር (በአዲስ አበባ) ከአረርቲ ደብረ ብርሃን ቀጥታ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡… የወረዳው ዋና ከተማ አረርቲ ትባላለች፡፡ አረርቲ ከተማ በከተማ አስተዳደርነት ከ 2012ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመች ሌላኝው የአረርቲ ከተማ አስተዳደር መቀመጫም ናት፡፡ አረርቲ ከሞጆ ደረቅ ወደብ እና የማሳለጫ አስፓልት መንገድ ለመድረስ በ 56 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗ ብዙዎች ለኢንቨስትመንት ልማት ተመራጭ ያደርጓታል፡፡ ከተማችን ያሉት የመንገድ ብቻ ሳይሆን በሰላሙም ጉዳይ የተረጋጋች መሆኗ እና ህዘቦቿ ባህል እና እምነታቸውን አክባሪ እንግዳ ወዳድ እና ተቀባይ መሆናቸው ከተማይቱን ላዩ ከገቡ ቡሃላ ለመውጣት ይቸገራሉ፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ከሚታወቅባቸው መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ የጤፍ አምራችነት ሲሆን ምንጃር ሽንብራ በብራንድ የተያዘለት ምርቱ ነው፡፡ የወረዳችን አፈር በዋነኝነት በእነኝህ ምርቶች ይታወቅ እንጂ መሬቱ የሰጡን የሚቀበል እና ምርት የሚሰጥ መሆኑ በየ ክረምት ወቅቱ የሚመረቱት የስንዴ፣ ሽንኩርት፣ ምስር፣ ቦለቄ፣ ማሾ፣ ማሽላ እና ሌሎች ምርቶች ይመሰክራሉ፡፡ ዚህን እውነታ ለማየት ክረምትን መጠበቅ አያስፈልጎትም፡፡ በቅዳሜ ቀን ወደ ከተማይቱ ሲዘልቁ ምንጃር ሸንኮራ ምን ያክል አምራች እና ቅዱስ ወረዳ መሆኗን ይገነዘባሉ፡፡ ወረዳችን በታሪኩም ቢሆን የተላላቅ አባቶቻችን መፍለቂያ የጀግኖች መኖሪያ መሆኗ አይዘነጋም፡- የአገራችን ምሁራን ስነሳ እነ ፀሀፍት አክሊሉ ሀብተወልድን፣ እነ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴን፣ እነ አፄ ዘርያቆብን ማንሳት ይቻላል የትውልድ ቀያቸው መነሻ ቦታቸው እዚሁ ምንጃር ሸንኮራ ነው፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በኃይማኖታዊ ክብሩ ባዕል በአገራችን ኢትዮጵያ በብቸኝነት የሚከበርበት “እግዚእነ ለሰንበት”/የደብረዘይት ክብረ ባዕል በገጠሪቱ ሳማ በሚባል ቀበሌ ሲሆን የሸንኮራው ቅዱስ ዮሃንስ ክብረ ባዕልን እና የፀበሉን ፈዋሽነት ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአንድነት የመስራት እና የትብብር ሁኔታውን ስናይ በእጅጉ ያስገርማል፡፡ ዘር ኃይማኖት የማይመረጥበት የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ መኖሪያ የሆነች ወረዳ ናት፡፡ የህዝቡን ትብብር እና አንድነት ለማየት መጠየቅም አያስፈልጎትም ብቻ ከአገራችን በዓይነቱ ለየት ተደርጎ በህዝብ ተሳትፎ እየተሰራ የሚገነውን የአረርቲዋን ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ግንባታ ማየት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ከዚህም ተጨማሪ ጉራንባ ማርያም ዶፋ ሚካኤል ባልጭ አማኑኤል ይገኙበታል ምንጃር ሸንኮራ በባህላዊ ጭፈራውም ይታወቃል፡፡ የባህል ጭፈራው እራስን ከማዝናናት ባለፈ የጋራ ስራቸውን በአንድነት የሚሰሩበትን ብሂል /ደቦ/ ለማከናወን የሚጠቀሙበት ስልት ነው፡፡  የወረዳው የቆዳ ስፋት፡- ስናይ 229,463 ሄክታር  የወረዳው አዋሳኞቹ ፡-  በሰሜን ሃገረ ማርያም ከሰም ወረዳ እና በረኸት ወረዳ  በደቡብ ቦሰት ወረዳ (ኦሮሚያ)  በምስራቅ በረኸት ወረዳ እና ፈንታሌ ወረዳ (ኦሮሚያ)  በምዕራብ ግንቢቹ ወረዳ (ኦሮሚያ)  የወረዳው መልከአ ምድር፡-  2% ተራራማ፣  84% ሜዳማ ፣  14% ወጣገባ ነው፡፡  የወረዳው አየር ንብረት፡-  4.3% ደጋማ ፣  70.9% ወይና ደጋ እና  24.8% ደግሞ ቆላማ ነው፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፡- በአሁን ሰዓት ለኢንቨስትመንት ምቹ ሆነች ወረዳ እና ሰላሟ የተረጋገጠ ከተማ መሆኗ ተመራጭ ያደርጋታል፡፡  የኢንዱስትሪ ፓርክ፡- ሴራሚክ ፋብሪካ፤ ጨርቃ ጨርቅ፤ የእንጨት ፋብሪካዎች  የማዳበሪያ ፋብሪካ  የፍራፍሬ እና አትክልት ምርጥ ዘር መፈብረኪያ እና ማዘጋጃ ፋብሪካ  የወተት እና የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ  ዘመናዊ የዶሮ እርባታ እና የከተማው አዲስ መንደር ግንባታ /ሪልስቴት/ እነኝህ በስራ ላይ ያሉ ፋብሪካዎች ሲሆኑ በቅርቡ ወደስራ የሚገቢ የመኖ ማቀነባበሪያ፤ የዱቄት ፋብሪካ ፣ሆቴል፣ኮሌጂ፣ሎጂ፣ ሆስፒታል ፣ተጨማሪ ሴራሚክ፣ አሳ እርባታ፣ ዶሮ እርባታ፣ ወተት፣ መስኖ፣ ግብርና ፣ የነዳጂ ዲፖ ፣መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ፣ ሶላር ኢነርጂ ፋብሪካ ፣የቁም እንሰሳ ፣ እና ሌሎቹም ይገኙበታል፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ለምን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሆነች 1. ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ያላት ርቀት አጭር መሆኑ፤ 2. ለደረቅ ወደብ በጣም ቅርብ መሆኑ 3. በክልላችን ብቸኛ የባቡር መስመር የሚያልፍበት መሆኑ፤ 4. በቅርብ ሊሰራ የታሰበው አረርቲ አዲስ አበባ መንገድ እውን ከሆነ 54 ኪ.ሜ በታች መሆኑ፤ 5. ህብረተሰቡ ልማት ወዳድ፣ ሰው አክባሪ እና ለሰላም ዘብ የሚቆም መሆኑ፤ 6. የተለያዩ ማዕድናት የሚገኙባት ወረዳ መሆኑ 7 የብዙ ቱሪስት መስህብ መሆኑ 8 ተፈጥሮአዊ የመሬቱ አቀማመጡ 9 አየር ንብረቱ ለሁሉም ተስማሚ መሆኑ 10 ከፍተኛ አምራች መሆኑ 11 ለሚፈልጉት ፋብሪካ ጥሬ እቃው ማዕድኑ ወይም ግብአቱ ብዛት እዚያው መገኘቱ 12 ከተማዋ ለሁሉም ክልሎች ቅርበቷ እናም ሌሎችም በርካታ ያልተጠቀሱ አስቻይ ሁኔታዎች ያሉባት ወረዳ መሆኗ ተመራጭ ያደርጋታል፡፡ እኛም እንደ ተቋም በዚች ውብ ከተማ የሪል እስቴት ግንባታን በመስራት ለከተማችን ተጨማሪ ውበት እና እድገትን እንጨምራለን ብለን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ሪልስቴታችን የሚገነቡትም 230,000ካሬ ሜትር ላይ ወይም 23ሄክታር ላይ ግዙፍ መንደር እንገነባለን ለኢንቨስት መንት እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ ላይ እየገነባን እንገኛለን ሪልስቴቱ ለአረርቲ ከተማ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሩዋል ሪልስቴቱ ላይ የተካተቱ 1ኛ ደረጃውን የጠበቀ 5*ሆቴል 2ኛ ደረጃውን የጠበቀ ከኬጂ እስከ ኮሌጂ 3ኛ ጤና ተቋም 4ኛ መዝናኛ ስፍራዎች 5ኛ መሠረተ ልማቶች የተሟሉ ውሃ፣ ኮብልስቶንመንገድ፣ ፣መብራት ።፣ ኮፓውድ አጥር የመሣሰሉት ያሉት ሲሆን ሪልስቴቱ ፦ የብሎክ አወራረዱ እና ሽንሻኖ ማለትም ከከፀሃይ አኳያ፣ ከውሃ ልክ ከዲዛይን፣ ቦታ አመራረጥ፣ለአስፋልት ያለው ቀረቤታ ፣ ለመኖሪያ የተመረጠ መንደር መሆኑ ተመራጭ አድርጎታል አጠቃላይ ወደሪልስቴቱ ደንበኛ ለመሆን ከፈለጉ 1ኛ ሪልስቴቱን ቢሮ ብቅ ይበሉ 2ኛ ወደ ሳይታችን ብቅ ብለው ይጎምኙ 3ኛ ለማንኛውም መረጃ 0912632430በሱፍቃድ 0910411282እጂነር ጌትነት 0940307878ዳውድ/ይደውሉ ለመመዝገብ እና አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ እሪልስቴታችን 150ካሬ 200ካሬ320ካሬ እንዲሁም 500ካሬ አዘጋጂተናል #አጠቃላይየ150ካሬ ቦታ ግንባታው 96ካሬ ላይ ያርፋል ሶስት መኝታ ቤት አለው 1ኛ አከፋፈሉም መጀመሪያ ቅድመ ክፍያ 2ኛ መታወቂያ ካርድ 3ኛ 3ት ምስክሮች 4ኛ የተርም ክፍያዎችን መዘጋጀት 5ኛ ስለሪልስቴቱ አገነባብ በሚገባ መረዳይሆናሉ ሶስት አይነት ግንባታ ቤቶች አዘጋጂተናል 1ኛ የቤቶዎን 50%ወይም ግማሽ እስከ ፓራፊት ድረስ ሙሉ ስመ ንብረት እስኪዞር ያለው ሽያጭ 1,200,000ነው 2ኛ ሁለተኛው ፊኒሽንግ የቀረው 1,580,,000ብር ነው 3ኛ ሙሉ ፊኒሽንግ የተጠናቀቀ ቤት 1,880,000ብር ነው ባለ 200ካሬ ቦታ አጠቃላይ ግንባታው 127ካሬ ላይ ያርፉል ባጠቃላይ ሁሉም ማህበረሰብ ወደከተማይቱ በመምጣት ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች ሁሉ በማዬት በተለያዩ ኢንቨስት መንት ላይ በመሰማራት ከተማችንን እንገባ ባሁኑ ሰአት ከተማዋ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች ሁሉ ምቹ ቅድመ ሁኔታ ያመቻቸ በመሆኑ መተው ኢንቨስት ያድርጉ! ኑ ከተማችን በጋራ እንገባ

Source: Link to the Post

Leave a Reply