You are currently viewing ምን ብዬ ልንገራት? በዘሪሁን ገሠሠ‼ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ #የመንግስታዊ_ክህደቱ_ማሳያ … ከነሀሴ 24 /2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ28 ተከታታይ ቀናት በሰማይና በምድ…

ምን ብዬ ልንገራት? በዘሪሁን ገሠሠ‼ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ #የመንግስታዊ_ክህደቱ_ማሳያ … ከነሀሴ 24 /2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ28 ተከታታይ ቀናት በሰማይና በምድ…

ምን ብዬ ልንገራት? በዘሪሁን ገሠሠ‼ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ #የመንግስታዊ_ክህደቱ_ማሳያ … ከነሀሴ 24 /2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ28 ተከታታይ ቀናት በሰማይና በምድር ጦር ተሞክሯል። 8 ጊዜ ፊት ለፊት ውጊያ ተካሂዶበታል ፣ 1 ጊዜ በጤፍ ውሃ በስተግራ በኩል በሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ፥ በመድፍና ቢኤም ፥ በሞርተርና በታንክ ፣ ….ወዘተ እሳት ዘንቦበታል ፤ ልዩ የኮማንዶ ጦር ገብቶ የሞት ሽረት ትንቅንቅ አድርጎበታል። ይሁን እንጂ የበላጎ ስትራቴጂክ ተራራዎችን ይዞ ለወራት እንደፍልፈል ምሽግ ሲቆፍር ፣ በኮንክሬት ሳይቀር ሲገነባ የነበረው የትግራይ ወራሪ ሀይል ከምሽጉ ንቅንቅ ሊል አልቻለም። …ሠራዊቱ ደከመ ፣ ተስፋ አስቆራጭ ሆነበት ፣ በምን አይነት ስትራቴጂ የላጎን ምሽግ መስበር እንዳለበት የሀሳብ ድሪቶ ማባዘቱን ቀጥሏል። ወደፊት ሲገሰግሱ ”ተመለሱ!’ የሚባለው የተለመደ የጦርነቱ ትራጄዲም እንደቀጠለ ነው። በዚህ መሀል እግር ተክለውና መሬት ሳይለቁ የሚዋጉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎችም ህልቆ መሳፍርት መስዋዕትነት እየከፈሉ ከመንግስት ጦር ቀድመው መዋደቃቸውን እንደቀጠሉ ናቸው። ነገርግን ፋኖዎቹ የበላጎ ምሽግ አይደፈሬነትና የመንግስት ጦር በዚህ ስትራቴጂካዊ ቦታ ተስፋ እየቆረጠ መምጣት ብሎም የተቀዛቀዘው የማጥቃት ሁኔታ እንደእግር እሳት ፈጅቷቸዋል። ይህን ምሽግ መስበር የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አምነዋል። የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈልም በሙሉ ልብ ቆርጠው ተነስተዋል። መስከረም 16/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ በላጎን ለመያዝ በበስተቀኝ በኩል በጥጃውሃ አቦ ቆርጦ የመግባት ድፍረት የተሞላበት የጦር ስትራትራጂ በመንደፍ ቅልጥ ያለው ውጊያ ተጀመረ። በተደጋጋሚ ሙከራ ተስፋው የተሟጠጠው የመንግስት ሰራዊት ከበላጎ ይልቅ በሌሎች አቅጣጫዎች ላይ በማተኮሩ ለበላጎ የተሰጠው ትኩረት እምብዛም ነበር። ነበልባሎቹ ፣ ምሽግ ደርማሾቹ ፣ ወፍ አርጋፊዎቹ የምስራቅ አማራ ፋኖዎች 24 ሰአት የፈጀ የሞት ሽረት ትንቅንቅ አደረጉ። የጠላት ምሽግ ላይ ዘለው ገቡበት ፣ ለወራት የመሸገውን የጠላት ጦር ሙትና ቁስለኛ አድርገው ረመረሙት ፤ እልህ አስጨራሹ የበላጎ ምሽግ ከረዥም ወራት በኃላ በምስራቅ አማራ ፋኖዎች ቁጥጥር ስር ወደቀ። ለወራት ያልተደፈረው አደገኛ ምሽግ ተደረማመሰ …! ይሁን እንጂ ተስፋ የቆረጠው የጠላት ጦር የተማረኩ የመከላከያ ሰራዊቶችን የደምብ ልብስ ለብሶ ከጀርባ በመምጣት አንጀቱን ባሳረሩት ፣ ለወራት የጨመደደውን ባስለቀቁት ፋኖዎች ላይ ጥቃት ሰነዘረ። በዚህ ጥቃትና በነበረው እልህ አስጨራሽ በጀብድ የተሞላ ትግል፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ በጦርነት ታሪኩ ከባድ የሚባለውን መስዋትነት ከፈለ ፤ ጀግናው አሸናፊ አለሙን ጨምሮ በርካታ የምስራቅ አማራ ጀግኖች በበላጎ ምሽግ ላይ ወደቁ …! ዋ! በላጎ…! ታዲያ በዚህ ውጊያ ከተሰውት ጀግኖች መካከል አሁን በስም የማልጠቅሰው ጀግና የፍም እሳት ወንድማችን ፣ መስከረም 15 እናቱን ደውሎ ካናገራት በኃላ ያቺ ድምፁ የመጨረሻው ሆነች። እናት ”ልጄ ሞቶም እንደሆነ ፣ በህይወትም ካለ እባካችሁ ቁርጤን ልወቅ !” የጧት ማታ ለቅሶና እዬዬዋ ሆነ። ከማውቃቸው ሰዎች ጋር እየሄደች በተደጋጋሚ ስታፈላልግና ስትጠይቅ በቅርበት አውቃለሁ….. እውነታውን ግን ልቤ ያውቃል …! የምስራቅ አማራ ፋኖ ያንን ሁሉ ተነግሮ የማያልቅ ጀብድ ፈፅሞ ”ጦርነቱ የስልጣን ግብግብነት መሆኑን በሚያሳብቅ መልኩ በፖለቲከኞቹ መተቃቀፍ ” ማብቃቱ ከተበሰረ በኃላ ፣ የሰማዕት ጀግኖቹን መርዶ ለቤተሰብ የማርዳት ፣ የቆሰሉትን የማሳከም ብሎም የጠፉትን የማፈላለግ ስራ ጀምሮ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሁኔታ ፣ ከጎኑ መስዋዕትነት የከፈለለት ኃይል ”በምስጋናና በሽልማት” ፋንታ ዙሮ ሊያጠቃው ጠብመንጃ አዙሮ ከበሩ ድረስ መጣ። መርዶ የማርዳቱ ተግባር ፣ ከዚች በር በር እያየች ቁርጧን ከምትጠብቅ እናት ጋር ሳይደርስ ፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ ዳግም በነፍሱ ከደረሰለት ሀይል ጋር ፣ የክህደት ጦርነትና ሰዶ ማሳደድ ውስጥ ገባ….! ይቺ የጀግና እናትም መርዶዋን ሳትሰማ ዛሬም እንባዋ ከጉንጯ ሳይደርቅ ፣ ”በር በር ….!” እያየች ልጇን በመጠበቅ ላይ ትገኛለች። ልጇ ጀግናና የሚያኮራ ታሪክ የፃፈ ሰማእት ቢሆንም ፣ በተለይ ለወላድ አንጀት ከባድ መሆኑ ግልፅ ነው። ግና ምን ልቤ በሀዘን ቢደማ ፣ ምን ብዬ ልንገራት ? ምንም! ነገ ታሪክ ተቀይሮ ከጀግኖቹ ጋር በጀግና ስነ-ስርአት እርሟን እንደምታወጣ ተስፋ አደርጋለሁ! በፋኖ ላይ ለሆነው ሁሉ ይህ አንዱ ልብን የሚያደማ ጉልህ ማሳያ ነው! አዎ! የክህደት ጥግ …..! አብሯቸው ድንጋይ የተንተራሰው ፣ የደማው የቆሰለው ፣ የተራበው የተጠማውን የምስራቅ አማራ ፋኖ ዙረው እንደጠላት በክህደት ሊወጉት በሩ ድረስ ሲመጡ ፣ የሰማእቶቹን መርዶ እንኳ በቅጡ አርድቶ ሳይጨርስ ነበር …! ክህደት‼️ ክህደት‼️ ክህደት‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply