You are currently viewing ምን እየሆነ ነው ? የምስራቅ አማራ ፋኖ ለአማራ ህዝብ እሴት ክብር ና ፍቅር አለን፣ የእለት ተእለት ኑሯችን  የሚመራበት የሞራል ህግ እንደ ሆነም ጥላትም ወዳጅም ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።ለማ…

ምን እየሆነ ነው ? የምስራቅ አማራ ፋኖ ለአማራ ህዝብ እሴት ክብር ና ፍቅር አለን፣ የእለት ተእለት ኑሯችን የሚመራበት የሞራል ህግ እንደ ሆነም ጥላትም ወዳጅም ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።ለማ…

ምን እየሆነ ነው ? የምስራቅ አማራ ፋኖ ለአማራ ህዝብ እሴት ክብር ና ፍቅር አለን፣ የእለት ተእለት ኑሯችን የሚመራበት የሞራል ህግ እንደ ሆነም ጥላትም ወዳጅም ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።ለማረክናቸው የጥላት ነፍሶች ፣ጓዶቻችንን ለነጠቁን ወራሪ አባላት የነበረን እርህራሄ ከበቀልነበት አማራዊ እሴት የመነጨ ነው። የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ተደራቢ ጥላት እና የትግል ሜዳ ላለመፍጠር ሲብል ብዙ ለግጭት የሚወተውቱ ጉዳዮችን እንዳላየን ተሻግረናል። የምስራቅ አማራ ፋኖ የትግል መሰረትና መግፍኤ ምክኒያት በህዝባችን ላይ የተጫነው የጭቆና ቀንበር እና ይፋዊ ወረራ ነው። ከዚህ ያለፈ የግል ጉዳያ የሚያሳስበን ከራሳችን የግል ፍላጎት ያልተላቀቅን ግለሰቦች አይደለንም። መላው ሠራዊታችን የተገነባበትና በልቦናው ያነገበው ዓላማ ከአማራ ህዝብ ፍላጎት የሚቀዳ የነፃነትና የእኩልነት የአትኩኝ ባይነት የነበረ የአባቶቻችን ውርስ ነው። ከዚህ አባታዊ መርህ ያፈነገጠ ተልኮ ኖሮት አያውቅም። ለባለፊት ተከታታይ ዓመታት በህዝባችን ላይ እና በሃገሪቱ የፀጥታ መዋቅር ወረራ እና ጥቃት የፈፀመውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ በተደረገው ትግል ከመንግስት ኃይሎች ጋር የነበረን ጥምረት፣ ያደረግነው ተጋድሎ ለሃገረ መንግስት እና ለመንግስታዊ ሥርዐት የከፈልነው ዋጋ ነው። ይኸ ትውልድ የአባቶቹ እሴት ለማስቀጠል እውጊያዎችን ለማስተፈስ ደሙን እንደ ሚያፈስና አጥንቱን እንደ ሚከሰክስ ያረጋገጥንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።ነገር ግን አማራ ዙሪያ ገባውን በጥላት እንደ ታጠረ የመዋቅራዊ ጭቆና ሰለባ እንደ ሆነ ጠፍቶን አይደለም። በሌላ መልኩ በአንድ ሃገር እና መንግስት ውስጥ ግጭትን በብቸኝነት የመቆጣጠር የህግ ኃላፊነት ያለበት ይኸን ግዴታ ለመወጣት የታጠቀ ኃይል የማደራጀት ሙሉ ስልጣን ያለው መንግስት እንደ ሆነ የአደባባይ የህዝብ እውቀት ነው። የመንግስት የፖለቲካ መዋቅር እና የፀጥታ ኃይል የትህነግን ወረራ መቋቋም ተስኖት መዋቅሩን እና እመራው አለሁ የሚለውን ህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉን ለምስክርነት ዛሬም በግዞት ላይ ያለው የራያ ህዝብ ህያው ምስክር ነው። የምስራቅ አማራ ፋኖ መንግስታዊ መዋቅር የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ ሆኖ የተደራጀ ህዝባዊ መዋቅር ነው። መንግስት ጦርነቱን በመዋቅሩ እንደ ማይቀለብሰው ተገንዝቦ ጥሪ ከማድረጉ በፊት በአባቶቻችን ወግ ቀድመን የተሰለፍን እና ጉዳዩ የገባን ሰዎች ነን። ከራያ ቆቦ እስከ ድሬ ሎቃ ፣ ከሀይቅ እስከ ቦሩ ስላሴ ፣ ከገነቴ እስከ መርከብ ተራራ ፣ ከጦሳ ተራራ እስከ ዞብል በተሳተፍንባቸው የደፈጣ እና የመደበኛ የግንባር ውጊያዎች ከአማራ ልዩ ኃይል እና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በጥምረት በጥላት ላይ ያሳረፍነው ምት ህመሙ ና ለምፁ አልተፋቀም። እንዲህ አይነቱ ለህዝብ እና ለሃገር እሴት የሚጨነቅ መች ኃይል በምትኩ የተሰፈረለት ክብር ና ሞገስ ሳይሆን አፈና እና በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ እሩምታ ነው። ይኸ ለምን ሆነ ብለን የምን ጠይቅ ሞኞች አይደለንም። እነማን ለምን አላማ እንደ ሚያደርጉት ግንዛቤው አለን። ህዝባችን ይልቁንም ያውቃል። ግን በጣም ፈጠነ። ሲጠቃላል በምስራቅ አማራ ፋኖ ወልደያ አዳጎ በሚገኘው የሎጅስቲክ መዐከል ና አመራሮች ላይ በዙ -23 ፣ በዱሽቃና በብሬን የታገዘ ድብደባ ሲደረግ አምሽቷል፤ዛሬም ልዩ ተልኮ ባላቸው የደቡብ ዕዝ አሃዶች. የሎጅስቲክ መዐከላችን የመዐከሉ ጠባቂዎች እና አመራሮች በከበባ ውስጥ ናቸው። የአማራ ህዝብ ምን እየተደረገ እንዳለ እና ቀጣዩ ፕሮጀክት ምን እንደ ሚመስል የማሳወቅ የሞራል ግዴታ ስለ አለብን እንጅ የመጣውን እንደ አመጣጡ. የማስተናገድ አባታዊ ውርስ ብቻ ሳይሆን ለባለፊት ዓመታት ያለፍንበት መንገድ እንደ ወርቅ ያነጠረን የትኛውም ጋጋት የሚያስደነግጠን ሰዎች አይደለንም። የአማራ ክልል መንግስት እና የሰሜን ወሎ አመራር የራሳችን ከህዝባችን መካከል እንደ አንዱ የምናያቸው ወንድም እና እህቶቻችን እንደ ሆኑ እናምናለን። ቀጣይ ተገማች የትግል ሜዳ የእነርሱን ሚና የሚሻ እንደ ሆነ እናስባለን። ማንዘጋውን አጀንዳ እየከፈትን ትግላችን ከመስመር ወጥቶ ህዝባችን ግራ እንዲጋባ ስለማንፈልግ መዘርዝር ውስጥ መግባት እንደ ማንፈልግ መግለፅ እንፈልጋለን። ነገር ግን በይቁም።አቅሉን የሚስትና ህዝባችን ጠባቂ አለኝ ብሎ ወደ ምኝታው ሲሄድ ባንኮኒ ተደግፎ አልኮን ውስጥ የሚዘፈቅ የፀጥታ መዋቅር አመራር አካባቢው ላለበት የደህንነት ስጋት እንደ ማይመጥን ሳናሳስብ ማለፍ አንፈልግም። በመጨረሻም የሎጅስቲክ መዐከላችን ዙሪያ የተጠመዱ የቡድን መሳሪያዎች እና ስምሪት የወሰደው አሃድ ይነሳ። የፋኖ አባላት እና አመራሮቻችን ላይ የሚደረገው ማዋከብ ይቁም። የምስራቅ አማራ ፋኖ ሃገርና ቀጠናው ወደ መደበኛ ሁኔታ ሲመለስ በህዝባችን ላይ የተቃጣው የህልውና አደጋ ሲቀለበስ ፣ ትህነግ ወደ መቃብር ሲወርድ ሰራዊታችን እና አመራሩ ወደ መደበኛ ሂወት እንደ ሚመለስ ማረጋገጥ እንሻለን!። የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለምታደርጉት ጥረት ክብር አለን። ለምታመጡት የመፍትሄ ሃሳብ ተገዥ እንደ ምን ሆን ማረጋገጥ እንሻለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply