ምክርቤቱ የአራት ሀላፊዎችን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20፣ 2013 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳ…

ምክርቤቱ የአራት ሀላፊዎችን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20፣ 2013 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት… አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡ በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሱትም፡- 1) አቶ አድጎ አምሳያ 2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ 3. አቶ ግርማ መኒ 4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረቡትን የ4ቱን የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ በደረሰው ሞት፣ ጉዳትና መፈናቀል እጅግ ማዘናቸውን የምክር ቤቱ አባላት መግለፃቸውን የቢሻንጉል ጉምዝ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል፡፡ ሌሎች የምክርቤት አባል ያልሆኑ አመራሮችም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የታወቀ ሲሆን፣ ብዙዎቹ አመራሮች በግድያ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ የክልሉ ፕሬዜዳንት ህግ እና ስራዓት ባለማስከበራቸው ከተለያዮ ወገኖች ወቀሳ እየተሰነዘረባቸው ቢሆንም፣ የብልጽግና ታማኝ ደጋፊ በመሆናቸው እስከ ስህተታቸውም ይምሩ የተባሉ ይመስላል፡፡ የተወሰኑ ሰዎችን በማሰር ብቻ የአመራር ለውጥ እና ህግ ካልተስተካከለ የመተከልን ሰላም ማምጣት አይቻልም፡፡ መተከል የአማራ እና የኦሮሞ የፖለቲካ ሽኩቻ ሜዳ ሆኗል ስለተባለ በነተስፋየ ቤልጅጌ እና መሰል የደቡብ ክልል አመራሮች በፌዴራሉ ውክልና እንዲመራ ተወስኗል፡፡ በመተከል የተፈናቀሉት ቁጥር ከ100ሺ በላይ ዘሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply