ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል፡፡

5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በስብሰባው የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ለመመደብ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የግልግል ዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓትን ለመደንገግ፣ የግብርና አምራችና አስመራች ግንኙነትን ለመወሰን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ይመራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

The post ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply