ምክር ቤቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ

አርብ ሀምሌ 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ከሰዓት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።

የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተሻሽሎ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት የሚያስችለው ተጨማሪ ስልጣንና ተግባር እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑን ተብራርቷል።

ከቃላትና ሀረጋት ብያኔ ጀምሮ በርካታ የአዋጁ አንቀጾች መሻሻላቸውንና አዳዲስ ሀሳቦች መካተታቸው ተገልጸዋል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1276/2014 አድርጎ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ አገራት ድርጅት የተቋቋመበትን የጆርጅታውን ሥምምነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡

በውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በዲማ ኖጎ (ዶ/ር) ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ አገራት ድርጅት (አካፓድ) የተቋቋመበት የተሻሻለው የጆርጅታውን ሥምምነት ረቂቅ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1277/2014 ሆኖ በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ መፅደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply