ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር በትግራይ ክልል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጽደቁን ተከትሎ ነው የመርማሪ ቦርድ አባላትን የሰየመው።

መርማሪ ቦርዱ 7 አባላት ያሉት ሲሆን፥ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከህግ ባለሙያዎች የተውጣጡ መሆናቸውም ታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

 1. አቶ ለማ ተሰማ- የቦርዱ ሰብሳቢ
 2. ወይዘሮ ጀምበርነሽ ክንፈ- ምክትል ሰብሰባቢ
 3. ወይዘሮ ሀዋ አሊ- አባል
 4. አቶ አለባቸው ላቀው- አባል
 5. አቶ ዘሪሁን ጴጥሮስ- አባል
 6. ወይዘሮ አስካለ ጥላሁን አባል
 7. አቶ ወንድሙ ግዛው- አባል ሆነው ተመርጠዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላቱን በ6 ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

የመርማሪ ቦርዱ ስልጣን እና ተግባርም፦

 1. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ግለሰቦችን ስም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግ እና የታሰሩበትን መክንያት መግለፅ።
 2. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢ ሰብአዊ እንዳይሆኑ መቆጣጠር እና መከታተል
 3. ማናቸውም የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢ ሰብአዊ መሆኑን ሲያምንበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት እርምጃውን እንዲያስተካክል ሀሳብ መስጠት።
 4. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢ ሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙት ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ።
 5. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንዲቀጥል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀርብ ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ማቅረብ ናቸው።

 

በሀይለኢየሱስ ስዩም

The post ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply