ምክር ቤቱ 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል

ምክር ቤቱ 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ ያካሄዳል።

የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ይመክራል።

በቀዳሚነትም የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያጸድቋል።

በመቀጠልም የጤና ሚኒስቴር አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች በተመለከተ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመጪው ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ ም አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ መሆኑንም ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ምክር ቤቱ 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply