You are currently viewing ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም በደረሰው የእሳት አደጋ የሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ይታወሳል፡፡

ባለስልጣናቱ ማምሻውን በአደጋው ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦችን ማጽናናታቸው ነው የተገለጸው።

በአደጋው በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና የንብረት ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን የገለጹ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከክፍለ ከተማውና ከወረዳው አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።

በወረዳው አየር አምባ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ህጻናት ሕይወት ያለፈ ሲሆን ሁለት ሰዎች ቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸው ህክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply