ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ በሃገሪቱ ባለው አሁናዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ መንግስት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ አንስተዋል፡፡

ችግሩ እዚህ ደረጃ እንዳይደርስ የፌደራል መንግስቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሄደባቸውን ርቀቶችም ጠቅሰዋል፡፡

በዋናነትም ፅንፈኛው ቡድን ህዝቡን ሽፋን በማድረግ የራሱን ጥቅም ሲያሳድድ መኖሩን እና ጥፋቶችን ሲያቀነባብር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

የነበረውን ሂደትም መንግስት በታላቅ ትዕግስት እና አስተዋይነት ሲመለከትና የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ነው ያነሱት፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶችና የትግራይ ክልል ተወላጆች ለሰላምና ለአንድነት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታወች ላይም እየመከሩ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለስ ዓለም ተገኝተዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

The post ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር እየተወያዩ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply