ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫን ጎበኙ

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫን ጎብኝተዋል።

የሀይል ማመንጫው አልፎ አልፎ የሚያጋጥመውን የግብዓት አቅርቦት እና የበጀት ችግር መቅረፍ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሀይል ማመንጫ በ32 ሄክታር መሬት ላይ በአመት 185 ጌጋ ዋት ሀወር የኤሌትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ሲሆን አሁን ላይ የገቢ አቅሙ ገና በመሆኑ ምክንያት የግብዓትና የበጀት ችግር እንደገጠመው የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ብሩክ ኤባ ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ምክትል ከንቲባዋ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታን የጎበኙ ሲሆን በውስጡ ያሉ ሰራተኞችን በገጠማቸው ችግሮች ዙሪያ አነጋግረዋቸዋል።

በዚህም የተለያዩ መሟላት የሚገባቸውን የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን ቦታው ከመጥበቡ የተነሳ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እየፈጠረ ስላለው ጫና ዶክተር እሸቱ ለማ የደረቅ ቆሻሻ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አብራርተዋል።

በጉብኝታቸውም ማጠቃለያ ምክትል ከንቲባዋ በተቋሙና አካባባው ላይ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ላሉ አካላት ያላቸውን ክብር በመግለፅ አስተዳደሩ በተነሱት ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ ለማምጣት አብሯቸው እንደሚሰራ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

The post ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply