ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ።
በዚህም ለሀገራዊ ልማትና ብልጽግና የግሉን ዘርፍ ሚና በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ÷ በግሉ ዘርፍ የተሰማራው ባለሀብት ፍትሀዊ ተወዳዳሪ ሆነው ለከተማዋ አጠቃላይ ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመዘርጋት እየተረባረበ ይገኛል ብለዋል።
ከፅንፈኝነት በመውጣትና አካታቹን የመሀሉን መንገድ በመከተል አገራዊ አንድነትን ለመፍጠርና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ሁሉም በተሰማራበት ጥረት እንዲያደርግም ምክትል ከንቲባዋ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው ÷ባለሀብቶቹ ከተሰማሩበት የኢኮኖሚ ሴክተር አንጻር ለሀገራዊ እድገትና ብልጽግና እያበረከቱት ያለው ተሳትፎ እና አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል ።
መንግስት አግላይነትን እያስወገደ ሀገራዊ ለውጡ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ለከተማዋ ብልፅግና ሚናውን እንዲወጣ የተጀመረው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ መለሰ አስገንዝበዋል።
ለግሉ ዘርፍ ማነቆ ሆነው የነበሩ በተለይም የኢንቨስትመንት አሰራሮችን፣ አዋጅና ደንቦችን በማሻሻል ለውጡ ከተማዊና ሀገራዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተንፀባርቋል።
በውይይቱ የተሳታፉ ባለሀብቶች በበኩላቸው÷ ከተማዋ በምታሳየው ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት የድርሻቸውን በማበርከት ለውጡን ወደፊት ለማራመድ እንደሚረባረቡ ገልጸዋል።
በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ለከተማዋ ዕድገት ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል የፊርማ ስነስርዓት መደረጉን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply