ምዕመኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 9 ቀን 2013…

ምዕመኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013…

ምዕመኑ የጥምቀት በዓልን ሲያከብር ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በቫይረሱ የሚያዙና ወደ ጽኑ ህሙማን የሚያመሩ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በዓላትን ተከትሎ በሚካሄዱ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች ሕዝቡ መዘናጋት በማሳየቱ ቫይረሱ በርካታ ሰዎችን በማጥቃት ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ነው ያነሱት። “በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ኅብረተሰቡ ይህንን ቸልተኝነት መድገም የለበትም” ያሉት ቀሲስ ታጋይ፤ ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በዓሉ በርካቶች የሚታደሙበት በመሆኑ ሁሉም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በማንኛውም ሥፍራ እንዲያደርግ አሳስበዋል ሲል ኢትዮ መረጃ ኒውስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply