
በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ዓመታት የኑሮ ውድነት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሻቅቧል። የሁሉም ምርቶችና አገልግሎቶች ዋጋ በብዙ እጥፍ ጨምሮ፣ የብር የመግዛት አቅም በእጅጉ አሽቆልቁሏል። በዓለም ላይ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ በአገር ውስጥ የተከሰተው ጦርነት እንዲሁም በዓለም ገበያ ያለው የነዳጅና የምግብ ምርቶች ዋጋ መጨመር ለዚህ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ግን ግን የዋጋ ንረትን እንዴት በቀላሉ ልንረዳው እንችላለን? መፍትሔውስ ምንድነው?
Source: Link to the Post