
ኢትዮጵያ ከውጭ መንግሥታት የተበደረችው ገንዘብ ለመጀመርያ ጊዜ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያለፈው እኤአ በ1981 ነበር። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ዕዳ በቢሊዮን ዶላሮች እየጨመረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት 56.6 ቢሊዮን ደርሷል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ይህንን ዕዳዋን የምትከፍለው ምን አስይዛ ነው? ባትከፍልስ የሚፈጠረው ምንድን ነው?
Source: Link to the Post