#ምጥ መቼ ይመጣል ፣ የሚስተዋሉ ምልክቶች? በምጥ የወለደች ፣ ለደቂቃዎች ያማጠች እናት፣ በምጥ የተያዘች የትዳር አጋርን በቅርበት ሆኖ ያየ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም የጤና ባ…

#ምጥ መቼ ይመጣል ፣ የሚስተዋሉ ምልክቶች?

በምጥ የወለደች ፣ ለደቂቃዎች ያማጠች እናት፣ በምጥ የተያዘች የትዳር አጋርን በቅርበት ሆኖ ያየ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም የጤና ባሞያዎች የምጥን ጭንቀት በየደረጃው የሚረዱት ይሆናል፡፡

በምጥ የተያዘችን ሴት ወደ ጤና ተቋም የሚወስድ የአንቡላንስ ሹፌር እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪም ቢሆን ህመሙ እና ጭንቀቱን ሲጋራም ይስተዋላል፡፡

የምጥ ፍሬው ክቡር የሆነ የፈጣሪ ስጦታ ልጅ ነው፡፡ ለወራቶች በማህጸኗ የተሸከመችውን ጽንስ፤ ጊዜው እና ሰዓቱ ደርሶ በእጇ ለመታቀፍ በመኖር እና በመሞት መካከል በእናት የሚከፈል መስዋትነት ቢባል ምን አልባት ሁኔታውን በትንሹ ሊገልጸው ይችላል፡፡

እርግዝናው የመጀመሪያ ከሆነ እና ስለ ምጥ ግንዛቤው ከሌለ የምጥ ምልክቶችን እንደ ህመም በማሰብ፤ ነፍሰጡር እናቶች ምጣቸውን ጨርሰው ወደ ጤና ተቋማት ሊሄዱ የሚችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

እርግዝና ከተፈጠረ ከመጨረሻ ሳምንታቶች በኋላ በአይን በሚታዩም ይሁን በማይታዩ ለውጦች ውስጥ በማለፍ ፤ ሰውነት እራሱን ለምጥ ያዘጋጃል ያሉን በቢጂኤን የእናቶች እና የህጻናት ልዩ ህክምና ሆስፒታል የማህጸን እና ጽንስ ስፔሻሊት ዶክተር እስክንድር ግዛው ናቸው፡፡

#ያለጊዜው ምጥ እንዲመጣ የሚያደርጉ ምክንያቶች

ብዙ ጊዜ ትኩረት ባይሰጠውም የጥርስ ህመም ያለ ጊዜው ምጥ እንዲመጣ ምክንያት እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

•የእናትየው እና በጽንሱ አፈጣጠር ምክንያት ያለጊዜው ምጥ ሊመጣ ይችላል
•በእርግዝና የመጨረሻ ሳምንት ላይ በሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አማካኝነት
•የእናት ወይም የጽንሱ ሁኔታ ላይ ችግሮች ካሉ በህክምና ያለ ጊዜው ምጥ እንዲመጣ ሊደረግ ይቻላል ተብሏል፡፡

#የምጥ ምልክቶች

•በእርግዝና ጊዜ ከ37ኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ 41 ሳምንት ድረስ ምጥ በየትኛውም ሰዓት የሚመጣ ይሆናል፡፡
•ከባድ የሆድ ቁርጠት
•ከባድ የሆነ የድከም ስሜት
•ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ መቀየር
•ፈሳሹ የደም የቀላቀለ መሆን
•የጀርባ ህመም
•ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

#እውነተኛ ምጥ ከውሸት ምጥ በምን ይለያል

•ከፍተኛ የሆነ የወገብ ህመም
• ከማህጸን ከዚህ ቀደም የተለየ ፈሳሽ መኖር ፤ፈሳሹ ደም የቀላቀለ መሆን
•የእንሽርት ውኋ መፍሰስ ይስተዋላል፡፡

የግዴታ ሶስቱም ምልክቶች በአንድ ላይ ባይስተዋሉም ሁሉም ተመጋጋቢ መሆናቸው ግን ተመላክቷል፡፡

#የውሸት ምጥ

• ለሰዓታት የቆየ ህመም ሊኖር ይችላል ያሉት ባለሞያው፤ ነፍሰጡር እናት የትኛውንም ምልክቶች ካስተዋለች ወደ ጤና ተቋማት መሄ ይገባታል፡፡ ምጡ እውነተኛ እና ውሸት ብሎ የሚለየው በዘርፉ ባለሞያ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በእርግዝና ወቅት አንዳንድ እናቶች የምግፍ ፍላጎት ላይኖራቸው የሚችል ቢሆንም፤ በአንዳንዶች ላይ ግን የምግብ ፍላጎት ሊጨምር ይችላል፣ እንቅስቃሴ አለማድረግ በተለያዩ ምክንያቶቾ የእናትየው ክብደት ሊጨምር እና ጽንሱ ሊፋፋ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

በዚህም ምክንያት የምጡ ሁኔታ እንዲከብድ እና እረዘም ያለ ጊዜን እናት በምጥ እንድታሳልፍ ምክንያት እንደሚሆን ይነገራል።

#ያለ ጊዜው ምጥ እንዳይመጣ ምን መደረግ አለበት

በእርግዝና ክትትል ወቅት ኢንፌክሽኖች ፣ ትኩሳት የሚያሚጡ ህመሞች፣ የጥርስ ህመም ካጋጠመ ህመሙን በማከም ምጡ ጊዜውን ጠብቆ እንዲመጣ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ያማጡበትን ቀን አለመርሳት አይደለም ለእናት ይቅርና በሰዓቱ አብረዋት ለነቡ ሰዎች ቢሆንም የማይዘነጋ ነው፡፡

ደም መፍሰስ ፣ የሆድ ህመም፣ የእንሽርት ውሀ መፍሰስ ምጥ ሊጀምር እንደሆነ ያመላክታል። የማያቋርጥ የጀርባ ህመም ካለ እና የጽንሱ እንቅስቃሴ ከቀነሰ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ የትንፋሽ ማጠር፣ እና ድንገተኛ የሰውነት ድካምን ያካትታል፡፡

በመሆኑም እናቶች የምጥ ምልክቶች ካስተዋሉ ምን አልባት የውሸት ምጥ ነው ከማለት ይልቅ ወደ ጤና ተቋማት እንደሚገባ የተናሩት ባለሞያው፤ የምጡን ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚቻለው በባለሞያ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply