ም/ጠ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለአምባሳደር ራይነር ሽኝት አደረጉ

ም/ጠ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለአምባሳደር ራይነር ሽኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ለነበሩት ማይክል ራይነር ሽኝት አድርገዋል።

ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል በኢትዮጵያ ስለነበራቸው ፍሬያማ ጊዜ አቶ ደመቀ ምስጋና አቅርበዋል ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለአምባሳደሩ በትግራይ ክልል እየቀረበ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ ፣ ስለመልሶ መቋቋም  እና የመሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታን በተመለከተ ገለፀ አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም በኢትዮጵያ በአዲሱ አስተዳደር በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች እና የአሜሪካ መንግስት ለዚህ ስኬት በነበረው አስተዋጽኦ ዙሪያም ምክር አድርገዋል።

ለአምባሳደር በቀጣይ ህይወታቸው ስኬት የተመኙት አቶ ደመቀ ኢረትዮጵያ በጆ ባይደን አስተዳደር ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ገልፀዋል

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ም/ጠ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለአምባሳደር ራይነር ሽኝት አደረጉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply