ም/ጠ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በንፁኃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ

ም/ጠ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በንፁኃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በንፁኃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ፡፡
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቀደም ሲል ብሄርን፣ ሃይማኖትን እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የማድረስ ዓላማ ያላቸው ጥቃቶችና ጭፍጨፋዎች መካሄዳቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው ባወጡት የሃዘን መግለጫ አስታውሰዋል፡፡
በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በንፁኃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደተፈፀመም ነው የገለፁት፡፡
በተለይ የአማራን ማህበረሰብ ትኩረት ያደረገና በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ ፍፁም አረመኔያዊና በፍጥነት መቆም ያለበት እኩይ ድርጊት ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ድርጊቱ አስቀድሞ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ ሲዘራ የቆየ በመሆኑ፤ ችግሩን የሚመጥን መፍትሄ በዘላቂነት ለማበጀት አስፈላጊው ሁሉ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡
ከዚህ አኳያ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ከሁሉም አቅጣጫ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመመከት የመንግስትና ህዝብ ቅንጅታዊ ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሩ የተሰማኝን ሃዘን እየገለፅኩ፤ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

The post ም/ጠ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በንፁኃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply