ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ ከእስራኤል የደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ ከእስራኤል የደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከእስራኤል የደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ።

ውይይቱ በዋናነት ረዥም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ትርጉም ባለው ደረጃ ማሳደግ ላይ ያለመ ነው ተብሏል።

ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ ይቫርካን በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች የጀመረችውን ለውጥ እስራኤል ትደግፋለች ብለዋል።

እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር በባህልና በቱሪዝም እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትሰራ ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር የጀመረችውን ግንኙነት ለማጠናከር መንግስት ቁርጠኛ እንደሆነ ጠቁመዋል።

እንዲሁም እስራኤል ለኢትዮጵያ እያደረገችው ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

The post ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ ከእስራኤል የደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply