#ሞላሌ መንደር ሙሉ በሙሉ ወደመ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አዋሳኝ…

#ሞላሌ መንደር ሙሉ በሙሉ ወደመ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም ግጭት ማገርሸቱ ይታወሳል። ግጭቱ የተከሰተው ከሸዋ ሮቢት ወደ ደሴ በሚያስኬደው መስመር ትንሽ አለፍ ብሎ ባሉት ቦታዎች ነው። ግጭቶቹ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ልዩ ስማቸው ጀጋኖ፣ ጀጀባ እና የለን መገንጠያ አካባቢዎች ቢሆንም ትናንት ምሽት ግን በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ስር ባለችው ሞላሌ መንደር ተስፋፍቶ ነበር። ከአስር ሺህ በላይ ነዋሪዎች ይኖሩባት የነበረችው ሞላሌ መንደር ሙሉ ሙሉ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተቃጥላ አድራለች። መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸው እነዚህ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ልመሰደድ ተገደዋል። እስካሁን ባለው መረጃ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከስምንት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የእማራ ልዩ ሀይል ትናንት ምሽት ላይ ውጊያው ወዳለባቸው አካባቢዎች በመግባቱ ዛሬ ምንም አይነት የቶክስ ልውውጥ አለመኖሩን ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጠናል። እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከወራት በፊት ህወሀትን ተከትለው የመጡት የሸኔ ታጣቂዎች ህወሓት ተመትቶ ሲመለስ የሸኔ ታጣቂዎች ግን ከነመሳሪያቸው በአካባቢው ተሸሽገው ቆይተው አሁን መልሰው ውጊያ መክፈታቸው ተሰምቷል። #Via,Roha Media ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply