You are currently viewing ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) ሀገር ወዳድ በሆኑትና በድርጅቱ የስዊድን ቻፕተር ስራ አመራርነት ባገለገሉት በመርከበኛ አቶ ከበደ ይመር ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለ…

ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) ሀገር ወዳድ በሆኑትና በድርጅቱ የስዊድን ቻፕተር ስራ አመራርነት ባገለገሉት በመርከበኛ አቶ ከበደ ይመር ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለ…

ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) ሀገር ወዳድ በሆኑትና በድርጅቱ የስዊድን ቻፕተር ስራ አመራርነት ባገለገሉት በመርከበኛ አቶ ከበደ ይመር ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻችው መፅናናት ተመኝቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በላከው የሀዘን መግለጫ ሀገር ወዳድ በሆኑት እና በድርጅቱ የስዊድን ቻፕተር ስራ አመራርነት ባገለገሉት በመርከበኛ አቶ ከበደ ይመር ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጧል፤ አያይዞም ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻችው መፅናናት ተመኝቷል። ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) እንደገለጸው በድርጅቱ የስዊድን ቻፕተር ስራ አመራርነት እና የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ በመሆን በቅንነትና በታማኝነት ያገለገሉት መርከበኛ አቶ ከበደ ይመር በ1950 ዓ.ም በደሴ ከተማ ነበር የተወለዱት። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በንጉስ ሚካኤል፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወይዘሮ ሲኂን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ተከታትለዋል። ገና የ 19 ዓመት ለጋ ወጣት እንዳሉም በኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ተኮትኩተው ስለማደጋቸው እና እስከ 1980 መጀመሪያ ድረስ በመርከበኛነት ስለማገልገላቸው ተገልጧል። አቶ ከበደ በስደት አገራቸው በስዊድን ኢትዮጵያዊያንን አስተባብረው እኤአ በ1989 ዓ/ም የመጀመሪያውን “የኢትዮጵያውያን ወዳጅነት ማሕበር”ን በማቋቋም ፋና ወጊ ነበሩ። አገራቸው ኢትዮጵያን በሚመለከትም ለድርድር ስለማያቀርቧት የዘር ፖለቲካውን በመቃወም ከጅምሩ ቆመው ለ 40 ዓመታት ታግለዋል። በስዊድን የሞረሽ ወገኔ የተመሰረተው እ ኤ አ 2014 ሲሆን አቶ ከበደ ይመር በስዊድን ቻፕተር የድርጅቱ ስራ አመራርና የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሆነው በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል። አቶ ከበደ በተከታታይ ለስድስት አመታት ያህል ያለማቋረጥ በሳምንት ሶስት ጊዜ ከ 600 እስክ 5000 ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ መረጃና ማስረጃ በኢሜል ይልኩ ነበር። አቶ ከበደ በኢሜል የሚልኩት ጊዜ ወስደውና መርጠው ጠቃሚ የሚሉትን፤ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ስለአማራው የህልውና ችግር ህዝቡ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያደርግ ሲሆን፤ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ጊዜ ድረስ ያለመታከት ያሰራጩ ነበር። አመለ ሸጋው አቶ ከበደ ቁምነገረኛ፣ ጨዋታ አዋቂ፣ አገር ወዳድ፣ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። አቶ ከበደ አንድ ልጅና ሶስት የልጅ ልጆች አሉዋቸው። የአቶ ከበደ ይመር የቀብር ስነስርዓት በሚኖሩበት ከተማ ጉተንበርግ Göteborg እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር የፊታችን አርብ የካቲት (februari) 25 ቀን 2022 ዓ.ም ሲሆን፤ በ 12:00 ሰዓት ስርዓተ ፍታቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በርይሾዳለን 44 (Bergsjödalen 44 )የሚከናወን ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱ ደግሞ በክቪበርግስ ሽርኮጎርድ (Kvibergs kyrkogård) ከቀኑ 14.00 ይፈፀማል። በመጨረሻም ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በአቶ ከበደ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ እየገለፀ እግዚአብሔር የአቶ ከበደን ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያስቀምጥልን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻችው መፅናናትን እንዲሰጥልን ሲል ተመኝቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply