ሞሪቴኒያ ውስጥ ጽንፈኛ እስላማዊ እስረኞች አመለጡ

https://gdb.voanews.com/EA85877D-BB28-4467-B750-5352949A9BE4_w800_h450.jpg

ሞሪቴኒያ ዋና ከተማ ኖክሾት ከሚገኝ ወህኒ ቤት አራት  ጽንፈኛ እስላማዊ  እስረኞች ማምለጣቸው ተገለጠ፡፡

ትናንት ዕሁድ ሌሊት እስረኞች ከወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች ጋር ተታኩሰው ሁለት የጥበቃ አባላት ሲገድሉ ሁለቱን ማቁሰላቸውን የአገር አስተዳደር ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ሁለቱ እስረኞች የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው እንደነበሩ እና ሁለቱ ደግሞ በሽብርተኛ ቡድን አባልነት ተከሰው ፍርዳቸውን እየጠበቁ የነበሩ ናቸው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply