ሞስኮ በጥቁር ባህር በኩል እህል እንዲወጣ የሚያደርገውን ሥምምነት እንድታድስ ተጠየቀ

https://gdb.voanews.com/66a4cc64-7376-4d59-bb6f-c832165a5502_w800_h450.jpg

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት እና የተመድ ዋና ጸሐፊ እህል በጥቁር ባህር ወደቦች በኩል ከዩክሬን እንዲወጣ ያስቻለውና ከሞስኮ ጋር የተደረሰው ሥምምነት እንዲራዘም ዛሬ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ኪየቭ ውስጥ የተገናኙት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የጥቁር ባህር ሥምምነቱ መራዘም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ጉቴሬዝ በበኩላቸው የምግብ ዋስትናን ለመጠበቅና የዓለም የእህል ዋጋን ለማረጋጋት የስምምነቱ መራዘም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው ሐምሌ በቱርክና በተመድ አደራዳሪነት ለ120 ቀናት የተደረሰው ሥምምነት ተቃዋሚ ከሌለ በፈርንጆቹ መጋቢት 18 ቀን ይታደሳል፡፡

ሥምምነቱ ከመቀጠሉ በፊት አገሪቱ ወደ ውጪ በምትልከው እህል ላይ የተደቀነው ጋሬጣ መነሳት አለበት ስትል ሞስኮ አሳስባለች፡፡

ሥምምነቱ ባለፈው ሐምሌ ከተፈረመ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እና ሌሎች በድርቅ ወደተጠቁ አገራት በመቶ ሺህ ቶን የሚቆጠር ስንዴ መላኩ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ስንዴ ተልኳል መባሉ በማጣጣል፣ አገሪቱ ስንዴ ወደ ውጪ ገበያ መላክ መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሲናገሩ  ተደምጠዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply