ሞደርና የማጠናከሪያ ክትባቱ የኦሚክሮን ቫይረስን ለመከላከል ውጤታማ ነው አለ

የዩናይትድ ስቴትስ መድሃኒት አምራች ሞደርና ሦስተኛው ዙር የሞደርና ክትባት መድሃኒት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ ለሚገኘው የኦሚክሮን ቫይረስ ውጤታማ መሆኑን በቤተ-ሙከራው በተደረገ ምርምር መረጋገጡን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ሞደርና በመግለጫው እንደማጠናከሪያ በግምሽ የሚሰጠው የክትባት መጠን የሰውነት የመከላከል አቅምን በ37 ጊዜ እጥፍ እንደሚያሳድግ ሲገልጽ ሙሉው ክትባት መድሃኒት ደግሞ 80 እጅግ የበለጠ አቅም የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡  

የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል መንግሥት የጤና ባለሥልጣናት ሁለቱም የሞደርናና ፋይዘር ክትባት መድሃኒቶች ለሁሉም አዋቂዎች እንደማጠናክሪያ ክትባት መድሃኒትነት ሊሰጡ የሚችሉ መሆናቸውን ባላፈው ወር መፍቀዳቸው ይታወቃል፡፡ 

የሞደርና መግለጫ የመጣው በዩናይትድ ስቴትስ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያ አንተኒ ፋውቺ ኦሚክሮን ቫይረስ በዓለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን በመጥቀስ ሁሉም አሜሪካውያን እንዲከተቡ ትናንት የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply