ሣልሳይ ወያነ ትግራይ (ሣወት) ብሔራዊ  ምርጫ ቦርድ  የጠየቀውን  ማብራሪያ   ለመስጠት እየተዘጋጀሁ ነው ሲል አስታወቀ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ባሳለፍነው ሰኞ ባወጣው መግለጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን አስመልክቶ ያሳለፋቸውን ውሳኔ ይፋ አድርጓል፡፡ከእነዚህ ውሳኔዎች መካከል በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት ፓርቲዎች ላይ በቦርዱ የትግራይ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በቀረቡ መረጃዎች እና ሌሎችም ጥቆማዎች መሰረት ተጨማሪ ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡

ቦርዱ ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ዓዴፓ)፣ ብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) እና ሣልሳይ ወያነ ትግራይ(ሣወት)  በክልሉ በተካሄደው ህገ ወጥ ምርጫ ላይ ስለመሳተፋቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡የሣልሳይ ወያነ ትግራይ (ሣወት) የህግ ክፍል ሐላፊ አቶ ተስፋዓለም በርሔ ከቦርዱ ጥያቄው እንደደረሳቸው ለአሐዱ አረጋግጠዋል፡፡ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡አሐዱ ከሣወት በተጨማሪ ባይቶናና ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለማነጋገር ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

**********************************************************************

ቀን 14/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ሣልሳይ ወያነ ትግራይ (ሣወት) ብሔራዊ  ምርጫ ቦርድ  የጠየቀውን  ማብራሪያ   ለመስጠት እየተዘጋጀሁ ነው ሲል አስታወቀ፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply