ሦስቱ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ! ታሕሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (…

ሦስቱ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ! ታሕሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ በዛሬው እለት ታህሳስ 27/2015 ዓ.ም ተፈራርመዋል። ፓርቲዎች ፊርማውን ያካሄዱት በራስ ሆቴል ራስ አዳራሽ ሲሆን በፊርማ ስነሥርዓቱ ላይ የየፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል። ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ ታኅሣሥ ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply