ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ከራስ ወዳድነት የሚያርቁበት ወር ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ገልጸዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲው ይህን ያሉት የታላቁ ረመዳንን ወር ፆም አስመልክቶ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ በመግለጫቸውም ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ የሚያርቁበት ወር ብቻ ሳይሆን መልካም በመስራት ራሳቸውን ከፈጣሪያቸው ጋር ይበልጥ የሚያቀራርቡበት ነው ብለዋል።

በመግለጫው የረመዳን ወር የበጎ አድራጎትና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርንም ይፋ አድርገዋል። መርሃ ግብሩ ይፋ የተደረገው በአፍሪካ ህብረት አጠገብ ለመስጂድ ግንብታ በተከለለው ስፍራ ሲሆን ድጋፉን ለሚያደርጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በተለይ ወቅቱ በጦርነትና በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገሪቱ የተፈናቀሉ እንዲሁም የሳውዲ ተመላሾች ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ያሉበት በመሆኑ የተለያዩ አካላት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መርሃ ግብር መሆኑ ተጠቅሷል።

ረመዳን ይቅር የምንባባልበት፣ ከ11 ወር ስህተታችን ወጥተን ወደ ፈጣሪ የምንቀረብበት፣ ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚያበላበት የራህመት ወር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ሙስሊሞች በዚህ የተቀደሰ ወር ተጠቃሚ እንድንሆን ራሳችንን ማስተካከል ይጠበቅብናል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply