ሩሲያ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቷን አስታወቀች፡፡የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ ሩሲያ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JMp3m2KSlGq1eZDUXHWEZqdbFHvFt2IxWEleE0p5w_VcOeMOCKT-6rkUg4VX6l5pdDLRUME4AO0l9e1jQqwhZHm0AeZOubzvSXsMrqifTJQ5xxhMdZSrCL5TyLs_y613Tsynw8j3iAFwZjITyLgopOp1K5U6cG6pKltCQxHbLOUXKZEcGcctI49I7OCQgZhV3Q-X_dDTFrXqSDDljRZPz0E73rPb7229Cqd1jquaRjaoV-EbcHigeyaNvxxch7wllFU7RwBIEvHskudN6F0By45q4js0GsJAJ75qWtrcNCIEcunszlA7hBPypJ4PtHZ9jKBQyiqxy7nSU65pOGl2iA.jpg

ሩሲያ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቷን አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ ሩሲያ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥታለች ብሏል።

በሩሲያ ኢምባሲ የፑሽኪን ባህል ማእከል አታሼ አልግዛንደር ኢቭቲግኒቭ ለኢትዮጵያዉያን የሚሰጠዉ የነጻ ትምህርት ዕድል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ብለዋል፡፡

በቅርቡም አንድ መቶ ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ የሩሲያ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡበትን ዝግጅት አጠናቀናል ነዉ ያሉት፡፡

የሩሲያ መንግስት በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሞስኮ ለኢትዮጵያውያን የምስጠዉ ነፃ የትምህርት ዕድል ኮታ 34 ብቻ እንደነበር ታወቋል፡፡

በቀጣይ አመት ደግሞ ቁጥሩን ከአንድ መቶ በላይ ከፍ ለማድረግ እንደሚሰራም አሌግዛንደር ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ከሶቭየት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያን በትምህርት ዘርፍ ስትደግፍ መቆየቷንም አስታውሰዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኘነት ለማጠናከር ከትምህርት በተጨማሪም በስፔስ ሳይንስ ዘርፍ ሩሲያ ድጋፍ እንደምታደርግ አንስተዋል፡፡

አባቱ መረቀ
ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply