ሩሲያ በሮኬት በፈጸመችው ጥቃት 51 ሲቪሎች ሞቱ

https://gdb.voanews.com/01000000-c0a8-0242-203f-08dbc63c0427_w800_h450.jpg

ከሩሲያ ትናንት የተተኮሰ ሮኬት፣ በዩክሬን ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኝ አንድ ካፌ ላይ ሲያርፍ፣ 51 ሲቪሎች መሞታቸውን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በቅርብ ወራት ውስጥ ከተፈጸሙት፣ በርካታ ሕይወትን የቀጠፈ ጥቃት እንደሆነ ተነግሯል።

ጥቃቱ የተፈጸመው የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ፣ 50 የሚሆኑ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች በስፔን በተገናኙበት ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት ነው። ዜሌኒስኪ በስብሰባው ላይ የተገኙት ሀገሪቱ ላለባት ጦርነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው። 

“የሩሲያን ጭካኔ የተሞላው ወንጀል የሚያሳይ፣” ሲሉ ጥቃቱን የገለጹት ዜሌንስኪ፣ “ሆን ተብሎ የተፈጸመ የሽብር ጥቃት” ነው ሲሉ አክለዋል።

“የሩሲያ ሽብር ሊቆም ይገባል” ያሉት ዜሌንስኪ፣ ምዕራባውያን አጋሮች ዩክሬን የአየር መከላከያዋን ማተናከር ትችል ዘንድ ድጋፍ እንዲያድርጉ ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply