የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠዉ መግለጫ፣ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ እርዳታ የተገነባዉን የሚሳዔል ሲስተም በሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሩሲያ ማዉደሟን አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም ሌሎች ሰባት በእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ የተደረጉ ሚሳዔሎች መጠለፋቸዉንም በመግለጫዉ አክሏል፡፡
በተያያዘ ዜና የሩሲያ የደህንነት መስሪያ ቤትን ስትሰልል አግኝቻታለሁ ያላትን ዩክሬናዊት ሴት ማሰሩ ተሰምቷል፡፡
የ25 ዓመቷ ዩክሬናዊት ወጣት የሩሲያ ወታደራዊ ሃይልን መረጃ አሳልፋ ሰጥታለች በሚል ነዉ የተከሰሰችዉ፡፡
ወጣቷ የቮስቶክ ባታሊዮንን ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ወታደራዊ አካሄድን በተመለከተ መረጃዎችን አሳልፋ ስትሰጥ ደርሼባታለዉ ያለዉ የሩሲያ መንግስት፣ ወዲያዉኑ እንድትታሰር በማድረግ የወንጀል መዝገብ ተከፍቶባታል ሲል አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post