ሩሲያ አሜሪካዊቷን እስረኛ ብርትኒ ግራይነር በልውውጥ ለቀቀች

https://gdb.voanews.com/022a0000-0aff-0242-f58b-08dad92f4c41_w800_h450.jpg

በሩሲያ ታስራ የነበረችው አሜሪካዊቷ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ኮከብ ብርትኒ ግራይነር በእስረኛ ልውውጥ መለቀቋን አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን አስታውቀዋል። 

አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያዊውን የመሣሪያ ሺያጭ ቪክተር ባውት በምትኩ ለቃለች። 

 “ከብርትኒ ጋር በስልክ ተነጋግሪያለሁ፣ ደህንነቷም የተጠበቀና ወደ ሃገሯም በመብረር ላይ ነች” ሲሉ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በትዊተር አስታውቀዋል። 

የሁለት ግዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ብርትኒ ግራይነር የካናቢስ ዘይት ይዘሻል በሚል ባለፈው የካቲት በሞስኮ አየር ማረፊያ መያዟ ይታወሳል። 

አደንዛዥ ዕፅ በሕገ-ወጥ መንገድ በማስገባት በሚል በሞስኮ የሚገኝ ፍ/ቤት ከ4 እስከ 9 ዓመት በሚደርስ እስራት ቀጥቷት ነበር። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply