
ሩሲያ እና ኩባ የአሜሪካን ጫና ለመመከት በጋራ እንሰራለን አሉ::
ሞስኮና ሃቫና ከዋሸንግተን የሚሰነዘርባቸዉን የኢኮኖሚ ጦርነት ለመመከት በቅንጀት እየሰሩ መሆናቸዉን በኩባ የሩሲያ አምባሳደር አንድሪ ጉስኮቭ አሰታዉቀዋል፡፡
አሁን ላይ የአሜሪካ መንግስት የሩሲያንና የኩባን የንግድ እንቅስቃሴ ለመግታት የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም ያሉት አምባሳደር ጉስኮቭ፣ ይህንን ሴራ ለማክሸፍ መፍትሄ እያፈላለግን ነዉ ብለዋል፡፡
ኩባ ላለፉት 60 አመታት በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማእቀብ የምትማቅቅ ሀገር ስትሆን፣ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ደግሞ ሩሲያ እጅግ በርካታ ማእቀብ የተጣለባት ሀገር መሆኗን የአር ቲ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
በአባቱ መረቀ
የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post