ሩሲያ የሚሳይል ጥቃቷን መባባሷ አይቀርም ተባለ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-996c-08db217b3ed4_w800_h450.jpg

ሩሲያ ትናንት ሀሙስ  የሚሳይል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ይበልጡን እየተደጋገመ መሄዱ እንደማይቀር አመልክቷል።

ትናንት ሩሲያ በተለያዩ የዩክሬን አካባቢዎች ላይ ብዛት ያለው ሚሳይል የተኮሰች ሲሆን  ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል። በመቶ ሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል።የትናንቱ የሚሳይል ጥቃት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከደረሱት ሁሉ ብዛት ያለው መሆኑ ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሀሙስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃል የሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የደህንነት ባለሥልጣናት የዩክሬኑ ጦርነት ወሳኝ ወቅት ላይ እየደረሰ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply