
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የልማት ጉዳይ ሆኖ ሳለ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረዉ የሚደረግ ጥረትን እንደምትቃወም ነው ሩሲያ ያስታወቀችው፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭግኒ ትረኪን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቀይታ፤በግድቡ ላይ መንግስታቸዉ ነፃና ገለልተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሞስኮ ከኢትዮጵያ፤ከሱዳንና ከግብጽ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላት የገለፁት አምባሳደሩ፤ግድቡን የፖለቲካ ጉዳይ ለማድረግ የሚደረገዉን ጥረት እንደማትቀበል አስታዉቀዋል፡፡
በዚህም ሩሲያ የግድቡ የድርድር ሂደት ወደ ፀጥታዉ ምክር ቤት ባመራበት ወቅት መቃወሟን አስታዉሰዋል፡፡
የሩሲያ መንግስት የኢትዮጵያን የልማት እቅድ እንደሚደግፍም ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም ሶስቱ ሀገራት በግዱቡ ዙሪያ ያላቸዉን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የቭገኒ ትረኪን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ የግድቡ ግንባታ 88 በመቶ መድረሱን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ማሳወቁ የሚታወስ ነዉ።
በአባቱ መረቀ
የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post