ሩስያ  አሜሪካ  የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ድርድርን ለመቀጠል ያቀረበችውን ሃሳብ ውድቅ አደረገች።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ   ሰርጌ ላቭሮቭ   ማንኛውም የሰላም ውይይት ከመጀመሩ በፊት ዩክ…

ሩስያ  አሜሪካ  የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ድርድርን ለመቀጠል ያቀረበችውን ሃሳብ ውድቅ አደረገች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ   ሰርጌ ላቭሮቭ   ማንኛውም የሰላም ውይይት ከመጀመሩ በፊት ዩክሬን ወደ ኔቶ ለመግባት የምታደርገውን ጥረት ማቆም አለባት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሩስያው ከፍተኛ ዲፕሎማት የዩናይትድ ስቴትስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ያቀረበችው ሀሳብ  ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እየሰጠች ባለችበት ሁኔታ የማይታሰብ  ነው ሲሉ ሃሳቡን   ውድቅ አድርገዋል።

ሰርጌ ላቭሮቭ በሰጡት መግለጫ ምዕራባውያን ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታጠናክር በማበረታታት የዓለምን ጸጥታ ስጋት ውስጥ ከተውታል   ሲሉ ከሰዋል፡፡

ምዕራባውያን ለዩክሬን ምንም አይነት  ድጋፍ ቢያደርጉ ሞስኮ ግቧን እንደምታሳካም  አስጠንቅቋል።

አሜሪካ በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዘርፍ ከሩሲያ ጋር  ግንኙነቷን ለማስቀጠል ባቀረበችው ሀሳብ ላይ አስተያየት የሰጡት ላቭሮቭ ሞስኮ የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓን ተናግረዋል።

መሰል ውይይቶች እንዲደረጉ በመጀመሪያ ዋሽንግተን በሩሲያ ላይ ያላትን ፖሊሲ ማሻሻል አለባት ብለዋል ሲል አልጀዚራ  ዘግቧል።

የውልሰው ገዝሙ

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply