ሩዋንዳ ለተባበሩት መንግስታት ተልእኮ 300 ወታደሮችን ላከች፡፡

ሩዋንዳ በመካከለኛዉ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ለማጠናከር 300 ወታደሮቿን ልካለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት በመጋቢት ወር 3ሺ ወታደሮችን አካቶ ማጠናከር ላይ አላማዉን ያደረገዉ እቅድ አንዱ አካል እንደሆም ተገልጻል፡፡

በአለም ደሀ ሀገራት ያሉበት የመካከለኛዉ አፍሪካ ሪፐብሊክ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2013 አ.ም ጀምሮ በእርስ በእርስ ግጭት መታመሱን እንደቀጠለ መሆኑም ይታወቃል፡፡

ሩዋንዳ የላከቻቸዉ ወታደሮች የመጀመሪያ ዙር እንደሆነ እና በካሜሮን ድንበር አካባቢ በባንጉይ እና በሎኮ መካከል ያለዉን ቦታ ለመጠበቅ የተላኩ ወታደሮች እንደሆኑ የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግስታት ሁለገብ የተቀናጀ ተልእኮ ቃል አቀባይ አብዱላዚዝ ፎል ተናግረዋል፡፡

ወታደሮቹ በተልእኮ ለአንድ አመት እንደሚቆዩ እና ሌሎች የሩዋንዳ ወታደሮች በአመቱ መጨረሻ እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-የሲጂቲኔ አፍሪካ ነዉ፡፡

ቀን 29/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply