ሩዋንዳ በኬኒያ የነበራትን ባንክ ዘጋች፡፡

ኬኒያ ውስጥ የነበረው የሩዋንዳ ባንክ ኦፍ ኪጋሊ መዘጋቱ ታውቋል፡፡
የኬኒያ ብሄራዊ ባንክ ከሩዋንዳ መንግስ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ባንኩ መዘጋቱን አስታውቋል፡፡

የኪጋሊ ባንክ በኬኒያ መዘጋቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ከዚህ በኃላ የዲጂታል ሞባይል ባንክ አገልግሎት ለመስጠት ካለን ፍላጎት የተነሳ ነው ባንካችን የዘጋነው ብሏል፡፡

በፈረንጆቹ 2013 የኬኒያ መንግስት ለውጭ ባንኮች ፍቃድ መስጠቱን ተከትሎ የተቋቋመው ባንክ ኦፍ ኪጋሊ ካከፉት አስራ አንድ አመታት በኬኒያ የባንክ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጻል፡፡

ባንክ ኦፍ ኪጋሊ በኬኒያ መንግስት ፍቃድ የተሰጠው ብቸኛው የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ባንክ እንደነበረም ነው የተገለጸው፡፡

ባንክ ኦፍ ኪጋሊ በሩዋንዳ መንግስት የሚተዳደር ሲሆን ባሁኑ ሰአት የንግድ ባንኮቹን ቁጥር እየቀነሰ ወደ ዲጂታል ባንክ አገልግሎት ፊቱን እያዞረ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply