ሪቻርድ ማስተርስ የሊጉ ሀላፊ የአርሰናልን ጨዋታ ይታደማሉ፡፡

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርሰናል ከኤቨርተን የሚያደርጉትን ጨዋታ ለመታደም መምረጣቸው ተገልጿል።

ሀላፊው በሲቲ ጨዋታ አለመታደማቸው በፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ክስ ላይ ለሚገኘው ማንችስተር ሲቲ አሸናፊ ከሆነ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን በእጃቸው እንዳይሰጡ እንደሚያደርጋቸው ተዘግቧል።

ሪቻርድ ማስተርስ ባለፈው አመት ኢትሀድ ተገኝተው የነበረ ሲሆን በዚህ አመት የማንችስተር ሲቲን ጨዋታ ለመታደም ሌላኛው ሀላፊ አሊሰን ብሪቴን እንደሚያመሩ ተነግሯል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply