ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን    REAL MADRID  CHAMPION በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን…

ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን    REAL MADRID  CHAMPION

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ካርቫል እና ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ስድስተኛ የሻምፒየንስ ሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በማሸነፍ በውድድሩ ታሪክ ቀዳሚው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ቪንሰስ ጁኒየር በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ሪያል ማድሪድ አስራ አምስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል።

በጋዲሳ መገርሳ

Source: Link to the Post

Leave a Reply