You are currently viewing ራሱን የቤኒሻንጉል ንቅናቄ ( ቤኒን) ፣የቅማንት ፅንፈኛ ሃይልና የትህነግ  ርዝራዦች  በቋራ  ዉጊያ ከፍተዉ   እነደነበር  የወረዳዉ አስተዳደር አስታወቀ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 18/2014/…

ራሱን የቤኒሻንጉል ንቅናቄ ( ቤኒን) ፣የቅማንት ፅንፈኛ ሃይልና የትህነግ ርዝራዦች በቋራ ዉጊያ ከፍተዉ እነደነበር የወረዳዉ አስተዳደር አስታወቀ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 18/2014/…

ራሱን የቤኒሻንጉል ንቅናቄ ( ቤኒን) ፣የቅማንት ፅንፈኛ ሃይልና የትህነግ ርዝራዦች በቋራ ዉጊያ ከፍተዉ እነደነበር የወረዳዉ አስተዳደር አስታወቀ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 18/2014/ አሻራ ሚዲያ ራሱን የቤኒሻንጉል ንቅናቄ ( ቤኒን) ፣የቅማንት ፅንፈኛ ሃይልና የትህነግ ርዝራዦች በቋራ ዉጊያ አድርገዉ እነደነበር የወረዳዉ አስተዳደር አስታወቀ የአማራ ልዩ ሃይል ፣ ፋኖ፣ ሚሊሻ፣እና ወጣቱ በጋራ በመቀናጀት ጠላትን ቅስሙን በመስበር ወደ መጣበት መመለስ ተችሏል ብሏል። በቀን 16/8/2014 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ክልል ዳንጉር ወረዳ ፍርጀ ሃሙስ በተባለ ቀበሌ በቋራ ወረዳ የሚኖሩ አርሶአደሮች ከብት ጠፍቶባቸው ከብት ለመፈለግ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ራሱን የቤኒሻንጉል ንቅናቄ ( ቤኒን) ፣የቅማንት ፅንፈኛ ሃይልና የትህነግ ርዝራዦች በከፈቱት ተኩስ በወገን ሃይል ሁለት ሰዎች ሲቆስሉ በጠላት ሃይል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ወደ መጣበት ተመልሷል ብሏል የወረዳዉ አስተዳደር ፡፡ ይህ የጥፋት ሃይል ዋናው አላማው አባይዳርን እና ባንባሆ ቀበሌን ለማጥፋት ቢሆንም በህዝቡ ከፍተኛ ተጋድሎ ዳር ደንበሩን ሳያስደፍር እየተከላከለ ቆይቶ ይህ ፀረ-ሰላም ሃይል በህዝቡ ብቻ የሚመከት ባለመሆኑ ወደ አባይዳር እና ወደ ባንባሆ ቀበሌ እንዳይገባና ጥፋት እንዳይፈፅም የአማራ ልዩ ሃይል ፣ ፋኖ፣ ሚሊሻ፣ፀረሽምቅ እና ወጣቱ በጋራ በመቀናጀት ጠላትን ቅስሙን በመስበር ወደ መጣበት መመለስ ተችሏል ፡፡ በዚህ የውጊያ ሂደት ጁንታው እና ተላላኪዎቹ ሲጠቀሙበት የነበሩት የቡድን መሳሪያ ዲሽቃ፣ቅንቡላ እና ስናይፐር ሲሆን ለመረጃነትም ውጊያው በተደረገበት ቦታ የተገኙ የተተኮሱና የከሸፉ ቅንቡላዎች ማሳያዎች ናቸው ብሏል፡፡ በመሆኑም መላው የወረዳችን ነዋሪዎች ይህንን ፀረሰላም ሐይል በመመከትና ቅስሙን በመስበር ወደ መጣበት እንዲመለስ ለአደረጋችሁት ታላቅ ተጋድሎ በወረዳው አስተዳደር ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለው ፡፡ አሁንም ይህ ፀረሰላም ሃይል ወደኋላ ቢያፈገፍግም አዘናግቶ ወደ ቀበሌያችን እንዳይመጣ ቁልፍና ንዑሳን በሮችን በመጠበቅ ፀጉረልውጥ ሃይል ሲኖር መረጃውን ለሚመለከተው የፀጥታ መዋቅር በማድረስ ሰላማችን እንዲረጋገጥ ምልዕክት እያስተላለፍኩኝ አሁን ባለንበት ሁኔታ ወረዳችን ፍፁም ሰላማዊ ስለሆነ ከጥበቃ ጎን ሁሉም ወደ የሥረው እንዲሰማራ ጥሪ አስተላልፋለው ፡፡ የተመደባችሁ የፀጥታ አካላትም ተልዕኮችሁን በአግባቡ እንድትወጡ ዕያሳሰብኩኝ መላው የቋራ ወረዳ ህዝብም ለዚህ ደጀን ለሆነን የፀጥታ የፀጥታ መዋቅር እስከአሁን ድረስ የምግብ እና የውሃ አቅርቦት እያደረጋችሁ ተገኛላችሁ፡፡ይህን ተግባራችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲሉ የቋራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ይርዳው ካሳሁን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመቀጠልም ዋና አስተዳዳሪው አያይዘው እንደገለፁት ይህ አይነት ትንኮሳዎች የቆዩ ስለሆኑ የሚመለከተው የቤኒሻንጉል ክልል እና የፌደራል ሐይል ይህን ጁንታና የጁንታው ተልዕኮ አስፈፃሚዎችን በአካባቢው በመገኘት የፍተሻና የማፅዳት ስራ በመስራት መጭው ወቅት የእርሻ ወቅት እንደመሆኑ መጠን አርሶ-አደሮቻችን ያላንዳች ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ አስፈላጊውን እርምጃ በጥፋት ሃይሉ ላይ እንዲወሰድ እና ቀጠናው የሰላም ቀጠና እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ሲል የዘገበዉ የወረዳው ኮምንኬሽን ነዉ፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply