You are currently viewing “ርሀብ በስንት ቀን ይገድላል እያልን የሞት ቀናችን እየተጠባበቅን እንገኛለን” የጻግብጂና የአብርገሌ ተፈናቃዮች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም…

“ርሀብ በስንት ቀን ይገድላል እያልን የሞት ቀናችን እየተጠባበቅን እንገኛለን” የጻግብጂና የአብርገሌ ተፈናቃዮች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም…

“ርሀብ በስንት ቀን ይገድላል እያልን የሞት ቀናችን እየተጠባበቅን እንገኛለን” የጻግብጂና የአብርገሌ ተፈናቃዮች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት ወደ አካባቢያችን ይመልሰን ሲሉ ከፃግብጅ ወረዳ ተፈናቅለው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በወለህ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ተናግረዋል። ነገሩ ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆነና ህይወት ውድ ናትና ውድ ህይወታቸውን ለማትረፍ ቢመጡም እስከወዲያኛው የፈሩት የሞቀ ቤታቸውን የለቀቁለት ጠላት በሶስተኛው ዙር ጦርነት ተከትሎ መጣና በርሃብ ኩርምት ብለው ከተጠለሉበት መጠለያ ሳይቀር አፈናቀላቸው፤ አቆሰላቸው፤ ገደላቸውም። አሁንም ድረስ ወደ አካባቢያቸው መመለስ ይቅርና ከበፊቱ በበለጠ በእርሃብ አለንጋ እየተገረፉ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ታዲያ ይህ የሰላም ስምምነት ለማን እንደሆነ እንቆቅልሽ የሆነባቸው ከፃግብጅና አበርገሌ ወረዳዎች በጦርነቱ ምክንያት ሀብት ንብረታቸውን፣ በግና ፍየሎቻቸውን በበረሀ በትነው፣ ሞፈርና ቀምበራቸው በግርብ ምስጥ በልቶባቸው ሁሉን ትተው በግድ ቀያቸውን ለቀው በሁለንተናዊ ችግር ውስጥ ሆነው መኖር ከጀመሩ እንሆ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። አቶ አብርሃ ወልዱ ይባላሉ የመጡት ከፃግብጅ ወረዳ ሲሆን የአምስት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ናቸው። እንደ እሳቸው ገለፃ ህይወት ገና ጊዜዋ ያልደረሰ ሁኖ እንጅ እንደ ችግራችን፣ እርሃብና ጥማችን ብዛት ቢሆን ኖሮ ህይወታችን አትኖርም ነበር አሁንም ነገን ዛሬ ልንሞት እያልን ነው ያልነው ሲሉ ችግሩን አጉልተው በሲቃ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በሴፍቲኔት ታቅፈው ይረዱ እንደነበርና ከሰኔ ወር ጀምሮ ግን የሴፍቲኔት እርዳታ እንዳልተሰጣቸው አክለው የገለፁት አቶ አብርሃ ህፃናት በእርሃብ እንዳይሞቱብንና የእለት ህይወታችን ለማሳደር አንዳንድ ግለሰቦች ላይ እየተበደርን ነው ህይወታችን እየመራን ያለነው ብለዋል። ሌላኛው ከመጠለያ ጣቢያው አግኝተን ያነጋገርናቸው የሁለት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ደባሽ በላይ አየለ ከፃግብጅ ወረዳ ተፈናቅለን ከመጣን ከአንድ አመት በላይ ሁኖናል፤ ኑሮአችን ችግራችን በጣም ከፍቷል ብሏል። በነበረው ጦርነት ሀብት ንብረታችን ቤታችን ትተን ነው የመጣነው ሲሉ በምሬት የተናገሩት ደግሞ ሰባት ቤተሰባቸውን ይዘው ከፃግብጅ ወረዳ ተፈናቅለው የመጡት ወይዘሮ ደበሱ በለጠ ሲሆኑ ከዚህ ከመጣን በኋላ የተወሰነ ድጋፍ እየተደረገልን የነበረ ቢሆንም ከመስከረም ወር ጀምሮ ግን ምንም አይነት እርዳታ እያገኘን አይደለም በዚህም በጣም ከፍተኛ ችግርና እርሃብ ውስጥ ላይ ነን ብለዋል። ተፈናቃዮቹ በቂ በሚባል ደረጃ እርዳታ እየቀረበላቸው አይደለም፤ ይህነን ጉዳይ ለመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ያለማቋረጥ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አልተገኘም። እናም ተፈናቃዩም ሆነ በሁለት ወረዳዎች ውስጥ ያለው በተለያዬ ምክኒያት ያልተፈናቀለው በባዶ ቤት መንግስት አልባ ሆነዋል ያሉት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን ናቸው። አቶ ሹመት አክለውም የእርሻ ጊዜ እየደረሰ ስለሆነ እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር ይህንን ተፈናቃይ ወደ ቀየው ለመመለስ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ያለ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ተፈናቃይ ወገኖቻችን በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በመጠለያና ከመጠለያ ውጭ ከ67 ሺ በላይ ተፈናቃይ ህዝብ እንደሚገኝ ከብሔረሰቡ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ምንጭ_ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply